አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ባለፉት 8 ወራት ከሸቀጦች ወጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ኢኮኖሚ ተኮር ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
በማብራሪያቸውም ከወጪ ንግድ አንጻር ባለፉት ስምንት ወራት ኢትዮጵያ ያገኘችው ገቢ ከየትኛውም ዓመት የኤክስፖርት ገቢ እንደሚበልጥ ገልጸዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ካቀረበቻቸው ምርቶች 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ነው የተናገሩት።
በሚቀጥሉት አራት ወራት ይህንን አስጠብቀን የምንሄድ ከሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ እመርታ ይመዘገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በ10 ዓመት ያስቀመጥነው ግብ እንደሚሳካም ማረጋገጫ ይሆናል ብለዋል።
ከሸቀጦች በተጨማሪ ከአገልግሎት ወጪ ንግድ 4 ነጥብ 7 ቢሊዮን፣ ከሬሚታንስ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን፣ ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 2 ቢሊዮን ዶላር በስምንቱ ወራት መገኘቱንም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል መንግሥት የሀገር ውስጥ ገቢና ታክስ መሰብሰብ አቅሙን እያሳደገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ባለፉት ስምንት ወራት ከ580 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገልጸዋል።
መንግሥት መሰረተ ልማት የሚያስፋፋው ገቢ መሰብሰብ ከቻለ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሌሎች ሀገራት አንጻር የሚሰበሰበው ገቢ አሁንም ዝቅተኛ ነው ብለዋል።
ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎች ጋር በመደራደር 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ ሽግሽግ እንደተደረገላትም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025