
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2017(ኢዜአ)፦የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ በቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ዙሪያ ያላቸውን የጋራ ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ በአፍሪካ ህብረት የአሜሪካ አምባሳደር ስቴፋን ሱሊቫን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
ውይይቱ የአፍሪካ ህብረት እና የአሜሪካ የቆየ ትብብር ማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን መለየት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው።
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነት ለሶማሊያ የሰላም እና መረጋጋት ጥረቶች ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል።
ለቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት በቁርጠኝነት መስራታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ከአፍሪካ ህብረት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026