
ደብረ መርቆስ፤ መጋቢት 22/2017(ኢዜአ)፡- በምስራቅ ጎጃም ዞን እስካሁን ከ13 ሺህ በላይ የተለያዩ የሃይል አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን የዞኑ ውሃና ኢነርጂ መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ተወካይ ሃላፊ አቶ አምበሉ መሰሉ ለኢዜአ እንደገለጹት አርሶ አደሩ በታዳሽ ሃይል የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ኑሮውን እንዲያዘምን በትኩረት እየተሰራ ነው።
በበጀት ዓመቱ የታዳሽ ሃይል አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ በተደረገው ጥረት እስካሁን ከ13ሺህ በላይ የሚሆነውን ማሳካት መቻሉንተናግረዋል።
ከቀረቡት የሃይል አማራጮች መካከልምየተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎች፣ በጸሐይ ሃይል የሚሰሩ ቁሳቁሶችና የባዮ ጋዝ ግንባታ እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።
በዚህም ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን አክለዋል።
የተለያዩ የሃይል አማራጮችን ተደራሽ በማድረግ የተከናወነው ተግባርካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ40 በመቶ በላይ ብልጫ እንዳለውም አስረድተዋል።
ውጤቱን ማስመዝገብ የተቻለው እየተሻሻለ የመጣውን የሰላም መስፈን በመጠቀም መንግስት፣ አጋር ድርጅቶችና አርሶ አደሮች በቅንጅት ባደረጉት ርብርብ መሆኑን አክለዋል።
ከአማራጭ የሃይል ምንጭ ተጠቃሚዎች መካከል በዞኑ የጎዛምን ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ትብለጥ አጥናፉ እንዳሉት በዚህ ዓመት የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ መጠቀማቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ለማገዶ ይወጣ የነበረው ወጪ ቀንሶላቸው ኑሯቸውን እንዳቀለለላቸው ገልጸዋል።
በዞኑ የደጀን ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ታምሩ ምረት በበኩላቸው በጸሃይ ሃይል የሚሰሩ የቤት መብራቶች እየተጠቀሙ እንደሆነ አስረድተዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026