
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 256/2017(ኢዜአ)፦በፈጠራ የሚመራ ኢኮኖሚ ለመገንባት የአዕምሯዊ ንብረት ስራዎችን ማሳደግ እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ገለፁ።
የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምር ውጤቶች የሆኑ 9 የፓተንትና ሁለት የዩቲሊቲ ሞዴል የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ምስክር ወረቀት ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ተረክቧል።
ሚኒስትር ዴኤታው በዚህ ወቅት እንዳሉት በመንግስት ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ የባዮ ኢመርጂንግ ነው።

ለምርምር ልማት ምቹ ስነምህዳር ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው አስፈላጊ የህግ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
ኢንስቲትዩቱ የምርምር ውጤቶችን በማውጣት ተኪ ምርቶችን በማምረት ለሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን በአለም ላይ በምርምር ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችል ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ለምርምር ግብዓት የሚሆኑ ሀገር በቀል ሀብቶች በሌላ እንዳይወሰዱ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲና የምርምር ተቋማት ከኢንዱስትሪው ጋር ውጤት እንዲያመጡ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ነው ያሉት።
እውቀትን መሰረት ያደረገ በፈጠራ የሚመራ ኢኮኖሚ ለመገንባት የፓተንት ስራን ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀው፤ መፍጠንና መፍጠርን ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት በትብብር እንሰራለንም ብለዋል።

የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ካሳሁን ተስፋዬ(ፕ/ር ) በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ የባዮ ኢኮኖሚ መሰረት ለመጣል የሚያስችል ምርታማነት የሚያሳድጉ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ዛሬ የአዕምሮ ንብረት ጥበቃ ያገኙት 11 ምርምሮች ከእነዚህ ስራዎች መካከል መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት የሚያስችል ነው ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ የምርምር ውጤቶችን ከማውጣት ባለፈ 435 የምርምሮችን በአለም አቀፍ ጆርናሎች ማሳተም መቻሉን አስረድተዋል።
ምርምር በእውቀት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም ለአገር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ተኪ ምርቶች ላይ በማተኮር ምርምር እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል እንደሚሉት የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ለቴክኖሎጂ ሽግግር ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ረገድ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የምርምር ስራዎች የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማግኘት ተኪ ምርቶችን ለማስፋፋትና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማበራከት የሚያግዝ ነውም ብለዋል።
በቀጣይም በአለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን የአዕምሯዊ ንብረት መፍጠርና ማስመዝገብ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026