
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ትራንስፖርት(ግሪን ሞቢሊቲ) እያከናወነችው ባለው ተግባር ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን አቅም እየፈጠረች መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በረኦ ሀሰን ገለጹ።
መንግስት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት በአጭር እና ረጅም ጊዜ እቅዶች በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በረኦ ሀሰን ለኢዜአ እንደገለፁት፤ መንግስት አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለማስፋፋት በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ የነዳጅ ትራንስፖርትን በኤሌክትሪክ ትራንስፖርት በመቀየር በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የማስፋፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ መሙያ ቦታዎችን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በአጭር እና በረጅም ጊዜ እቅድ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ መገጣጠም የሚያስችል ስትራቴጂ ተቀርጾ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ ማምረት የሚያስችል የተፈጥሮ ሀብት ያላት በመሆኑ ሀብቱን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ ለማምረት በረጅም ጊዜ እቅድ እየሰራች እንደምትገኝም ሚኒስትር ዴኤታው አመላክተዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ተቋማት ሃብታቸውን እንዲያፈሱ ብሎም ልምዳቸውን እንዲያጋሩ መድረክ እየተፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ኢትየጵያ ከ700 በላይ የአለም አቀፍ ተቋማትና ኤክስፖርተሮች እና አመራሮች የተገኙበት በአረንጓዴ ትራንስፖርት ላይ ያተኮረ አለም አቀፍ ኮንፍረንስ ማካሄዷንም ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ትራንስፖርት(ግሪን ሞብሊቲ) ላይ እያከናወነች ባለችው ተግባር ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን አቅም እየፈጠረች መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
የህዝቡን ሰፊ የትራንስፖርት ጥያቄ ከመመለስ አንጻር ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የኤሌክትሪክ መኪኖችን የመገጣጠም ስራ ትኩረት የተደረገበት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026