
አዲስ አበባ ፤መጋቢት 26/2017(ኢዜአ)፦ መጋቢት 24 የትልሞቻችን ሁሉ የስኬት ጫፍ መጀመሪያ፣ የለውጥ ጮራ መባቻና የብልፅግና ዘመን ጅማሮ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሰባት የለውጥ ዓመታትን በድል ተሻግረን የሰነቅናቸውን ታላላቅ ሕልሞች እያሳካን፣ የገጠሙንን ፈተናዎች ከህዝባችን ጋር በቅንጅት በመስራት እየተሻገርን፣ የመዳረሻ ተስፋዎቻችንን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን እየቀየርን እና ለህዝባችን የሚበጁ አያሌ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል።
መጋቢት 24 የትልሞቻችን ሁሉ የስኬት ጫፍ መጀመሪያ፣ የለውጥ ጮራ መባቻና የብልፅግና ዘመን ጅማሮ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በብልፅግና ዘመን ስብራቶቻችንን የሚጠግኑ፣ የምናባችንን ከፍታና የተስፋዎቻችን ጥልቀት የሚመጥኑ የለውጥ ስራዎች ጥልቀትና ጥራት ባለው መልኩ በከተማና በገጠር እየተከናወኑ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
መዳረሻዎቻችን ከመንገዶቻችን ጋር የተሰናሰሉ፣ የህዝባችንን ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጣቸውን የሚመሰክሩ የለውጥ አሻራዎች ህያው ማሳያ ከተሞቻችን መካከል ደሴ አንዷ ናት በማለት በማሳያነት ጠቅሰዋል።

በደሴ ከተማ ከቧንቧ ውሃ አደባባይ እስከ ወሎ ባህል አምባ የሚደርስ 1 ነጥብ 89 ኪሎ ሜትር የሚሸፍንና 46 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ያለው የኮሪደር ልማት፣ ቅልጥፍናና ጥራትን የሚጨምር፣ አገልግሎትን የሚያሳልጥ እንዲሁም ደህንነትን የሚያስጠብቅ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትና ሌሎችም ተጠቃሽ የልማት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026