አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ለማዘመንና ለማሳደግ የሚከናወኑ ተግባራትን በመደገፍ ከዘርፉ ተዋናዮች ጋር በቅርበት እንደሚሠራ የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙአዝ በድሩ(ዶ/ር) ገለጹ።
ባለስልጣኑ ከኤች.ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር የግንባታ ጥራትን ማስጠበቅ የሚያስችል ቴክኖሎጂ የማስተዋወቅ መርሃ ግብር አካሂዷል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙአዝ በድሩ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ባለስልጣኑ ለዘርፉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ የግል እና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ዕድገት ሚናቸውን እንዲወጡ እየሰራ ነው።
ምርትን ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ጠንካራና ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎች መገንባት የሚቻለው ወደ ሀገር የሚገባ ምርትን የሚተኩ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የኮንስትራክሽን ዘርፉ በኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት ውስጥ ድርሻው የጎላ እንደሆነም ነው የጠቀሱት።
በዚህም ዘርፉ ወደ ዘመናዊነት እንዲሸጋገር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅና የማቅረብ ተግባር እየተከናወነ ነው ብለዋል።
የግብዓት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ማሟላት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።
ለአብነትም ዛሬ የተዋወቀው አዲስ የፕላስቲክ ጥሬ እቃ እና በወዳደቁ የፕላስቲክ ውጤቶች መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል የሚሰራው ፎርምወርክ(የግንባታ ኮንክሪት ቅርጽ ማውጫ) ለዘርፉ መጎልበት ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል።
ምርቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደግፎ የሚመረት በመሆኑ በዘርፉ ያለውን የኮንስትራክሽን ግብዓት ችግር ለመፍታት ከማገዙ ባለፈ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጪ ምንዛሬን ማዳን ያስችላል ነው ያሉት።
የኤች.ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩ ዊርቱ፥ የፕላስቲክ ፎርምወርክ የግንባታ ዘርፉን ተወዳዳሪነት እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ኢሳያስ ገብረዮሃንስ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የፕላስቲክ ፎርምዎርኩ ለህንፃ ግንባታ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎች የሚያስፈልግ ግብዓት ነው ብለዋል።
የኮንስትራክሽን ግብዓት የጥራት ችግርን የሚያቃልል እንደሆነም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025