
ጎንደር፤መጋቢት 28/2017(ኢዜአ)፡-በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች ኢንቨስትመንትን በመሳብና ቱሪዝሙን በማነቃቃት የጎላ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
የከተማውን የንግድና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚያግዝ የምክክር መድረክ ዛሬ በጎንደር ተካሂዷል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በከተማዋ እየተገነቡ የሚገኙት የኮሪደር ልማቱና የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳት ኢንቨስትመንትንና የቱሪዝም ፍሰቱን ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲሸጋገር ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ ለአንድ ታዋቂ ባለሀብት በአንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚያስገነቡት ዘመናዊ ሪዞርት ግንባታ የሚውል ቦታ በመስጠት ወደ ስራ የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸቱን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
ወደ ከተማው የመጡ በርካታ የልማት እድሎች በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቀው የከተማዋን እድገትና የህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
ህዝቡ በሰፈርና በቀበሌ ተደራጅቶ ሰላሙን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለው ተሳትፎ ለልማቱ አጋዥ እየሆነ መምጣቱን ጠቁመው፤ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የከተማው የኮሪደር ልማት ስራ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ንግድን በመቆጣጠርና ስርዓት በማስያዝ ዘመናዊ ግብይት እንዲሰፍን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ያሉት የከተማው ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ናቸው፡፡
ከተማውን ለመቀየር እየተደረጉ ያሉት የልማት ጥረቶች ለንግዱ ማህበረሰብ ምቹ የንግድ እንቅስቃሴ ከመፍጠሩም በላይ በነበረው ችግር ተቀዛቅዞ የቆየው የከተማውን የንግድ እንቅስቃሴ ማነቃቃት ማስቻሉን ጠቁመዋል፡፡
የከተማውን የንግድ እንቅስቃሴ በስርዓት ለመምራት እንዲቻል በከተማ አስተዳደሩና በክልሉ የበጀት ድጋፍ በ160 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተከናወነ የሚገኘው ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከመድረኩ ተሳታዎች መካከል የሱቅና የመኪና ጥበቃ ማህበር አመራር አባል ወጣት እባበይ በሰጠው አስተያየት፤ የኮሪደር ልማት ስራው ለማህበሩ አባላት ምቹ የስራ እድል እንደፈጠረላቸው ተናግሯል፡፡
የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች መንግስት በአግባቡ ምላሽ እየሰጠ በመሆኑ እኛም ልማቱ እንዳይደናቀፍ ሰላማችንን የመጠበቅ ግዴታችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን ብሏል፡፡
የከተማው አውራጅና ጫኝ ማህበር አመራር አባል ግርማቸው መኮንን በበኩሉ፤መንግስት የህግ የበላይነት በማረጋገጥ ያከናወናቸው ተግባራት የዕለት ተዕለት ስራችንን በአግባቡ እንድናከናውን ረድቶናል ሲል ገልጿል።
በመድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ፣የአውራጅና ጫኝ የደላሎችና የፓርኪንግ ጥበቃ ማህበራት አመራርና አባላት ተሳትፈዋል፡፡
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026