
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለመፍጠር በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ።
በጃይካ ከፍተኛ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አማካሪ አቱሺ ያማናካ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝቷል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) ለልዑኩ አቀባበል በማድረግ ተቋሙ እየተገበራቸው ያሉ ሁሉን አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕቀፎች የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ጉብኝቱ ኢትዮጵያ እና ጃፓን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ለሀገር ልማት ለመጠቀም ያላቸውን የትብብር ቁርጠኝነት በግልጽ የሚያመላክት ነው ብለዋል።
የጃይካ ልዑክ ለኢንስቲትዩቱ ስኬቶች አድናቆታቸውን መቸራቸውን ከኢኒስቲትዩቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ሁለቱ ተቋማት የሀገር በቀል ቋንቋ አጠቃቀም፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለግብርና እና ለኢንስቲትዩቱ የክህሎት ልማት ኢኒሼቲቮች መጠቀም ላይ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውም ተጠቁሟል።
የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ(ጃይካ) ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ በኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶችና ዓለም አቀፍ ትብብር ላይ እየሰራ ይገኛል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026