የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በክልሉ በአሲዳማነት የተጠቃ መሬትን በማከም የአፈር ለምነትን ለመመለስ እየተሰራ ነው - የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

Apr 9, 2025

IDOPRESS

መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ህዝቦች ክልል በአሲዳማነት የተጠቃ 800 ሺህ ሄክታር መሬትን በማከም የአፈር ለምነትን ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል አለሙ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ ከሚታረሰው መሬት ውስጥ 800ሺህ ሄክታር የሚሆነው በአሲዳማነት የተጠቃ ነው።

ይህም በምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ስላልው ችግሩን ለመፍታት ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተለይ አሲዳማ አፈርን በኖራ፣ በቨርም ኮምፖስት፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ማዳበሪያ የማከም ሥራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ነው የገለጹት።

ከኢትዮዽያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀትም አሲዳማ አፈርን መቋቋም የሚችሉ የሰብል ዝርያዎችን ለማላመድም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

በአሲዳማነት ችግር ምርታማነታቸው የቀነሱ መሬቶችን በሻይ ቅጠልና በቡና ልማት ለመሸፈን ክልላዊ ኢኒሼቲቭ ተቀርጾ ወደ ትግበራ መገባቱንም አቶ አማኑኤል አውስተዋል።


በኢትዮዽያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአፈርና ውሃ ምርምር ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ(ዶ/ር) በበኩላቸው እንደ ሀገር የአፈር አሲዳማነት ችግርን በዘላቂነት በመፍታት ምርታማነትን ለማሳደግ መሰራቱን ጠቁመዋል።

ለእዚህም ኢንስቲትዩቱ በየደረጃው ከሚገኙ የክልል ግብርና ምርምር ተቋማት፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተለይም የሚሰጡት ምርት የቀነሱ መሬቶችን በቪርሚን ኮምፓስትና በኖራ በማከም የአፈሩን ለምነት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

የአፈር አሲዳማነት ችግር ስጋት ሆኖ እንዳይቀጥል ዘላቂ የአፈር ለምነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅም ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025