የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በአፋር ክልል የአፈርና ውሃ ጥበቃና እንክብካቤ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

Apr 9, 2025

IDOPRESS

ጭፍራ፣ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል የአፈርና ውሃ ጥበቃና እንክብካቤ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዓሊ መሐመድ ገለጹ።

የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ የሚያስችል የምክክር መድረክ በአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳ በመካሄድ ላይ ይገኛል።


መድረኩን ያስጀመሩት አቶ ዓሊ እንዳሉት የዛሬው መድረክ በአገር ደረጃም ሆነ በክልሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ የሚደረጉትን ጥረቶችን የሚያግዝ ነው።

የተጀመረው የአፈር ጥበቃና እንክብካቤ ስራ በቀጣይነት ማጠናከር ክልሉ በምግብ ራሰን ለመቻል በሚያደርገው ርብርብ ውሰጥ አዎንታዊ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።

በክልሉ ደረጃ የተጀመሩትን የልማት ስራዎች ለማስቀጠልና ያሉትን መሬቶች ወደ እርሻ ስራዎች ለማስገባት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

በክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ኡስማን መሐመድ በበኩላቸው እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት ለአፈርና ውሃ ጥበቃ እና እንክብካቤ ሥራ ትኩረት በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እየተሰራ ነው።


ይህም መሬትን ለእርሻ ስራ እንዲያመች በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በዚህ ዓመት በክልል ደረጃ በ10 ወረዳዎች ላይ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከእነዚህ ውሰጥ ሞዴል በሆነው ጭፍራ ወረዳ ገሪሮ ቀበሌ ላይ ከ2 ሺህ 400 ሄክታር በላይ የማገገሚያ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህም ከሁለት ሺህ በላይ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ የተራቆተውን መሬት ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚያስችል የንቅናቄ መርሃ ግብር ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በተገኙበት መጀመሩን አስታውሰዋል።

ይህ ክንውን በምግብ ራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት አጋዥነት ያለው መሆኑንም አመላክተዋል።

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ባዘጋጀው በዚሁ መድረክ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ከግብርና ሚኒስቴርና ከአካባቢ ጥበቃ ባለ ስልጣን ፤ ከግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመጡ ተወካዮችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025