
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፦ለወሎ ተርሸሪ ኬር የህክምና እና የማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ የተሰበሰበ ገንዘብና ንብረት የፋይናንስ ኦዲት በማከናወን እስከ ግንቦት 15 ድረስ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ርክክብ እንዲፈፀም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የወሎ ተርሸሪ ኬርና የማስተማሪያ ሆስፒታል ፕሮጀክት በጎ አድራጎት ኮሚቴ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱን ለመዝጋት የሚደረግ የገንዘብና የንብረት የቅድመ ርክክብ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በመድረኩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ (ዶ/ር)፣ የኢፌዴሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን ቢራቱ፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አወል ስዒድ (ዶ/ር) የወሎ ተርሸሪ ኬር እና የማስተማሪያ የወሎ ሆስፒታል በጎ አድራጎት ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ጣይቱ ዓሊ እና የአከባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርሲቲው የወሎ ተርሸሪ ኬር የህክምና እና የማስተማሪያ ሆስፒታል ስም የተሰበሰበ ገንዘብ እንዲረከብ ከወራት በፊት በምክር ቤቱ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ይህንንም እንዲያስፈፅም የኢፌዴሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ኃላፊነት እንደተሰጠው ተናግረዋል።
በዚህም የክዋኔ ኦዲት መደረጉን አንስተው፤ በቀጣይ ጊዜያት የፋይናንስ ኦዲት በማከናወን እስከ ግንቦት 15 ድረስ የገንዘብና ንብረት ርክክብ እንዲፈፀም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026