የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

Apr 9, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተውን ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ቢሮ የኢኮኖሚ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ ሳይመን ሞርዱ ከተመራ የህብረቱ የከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑካ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚ ልማት፣ በንግድ እና በኢንቨስትመንት ያለውን ተሳትፎ በማሳደግ የሁለቱን ወገኖች ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።

ምክክሩ ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት ትብብራቸውን የጀመሩበት 50ኛ ዓመት እና በቅርቡ ከተፈራረሙት አዲስ ስምምነት ጋር መገናኘቱ ሁለቱ ወገኖች ትብብራቸውን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያመላክት ተገልጿል።

የአውሮፓ ህብረት በመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ላይ ትኩረቱን ባደረገው "Global Gateway" ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ መሆን በምትችልበት ሁኔታ ላይም ምክክር ተደርጓል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ለልዑኩ ስለ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ማሻሻያው የግሉ ዘርፍ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እና የኢኮኖሚ ድርሻ ማሳደግ አበይት ትኩረቱን ማድረጉን ገልጸዋል።

ቴሌኮምን ጨምሮ ከዚህ በፊት ለውጭ ኢንቨስትመንት ዝግ የነበሩ ቁልፍ መስኮችን ክፍት ማድረግን ጨምሮ እየተተገበሩ ያሉ ማዕቀፎች የንግድ ስራ ምቹነትና የኢንቨስትመንት ከባቢ አየር ለመፍጠር አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመዋል።

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ቢሮ የኢኮኖሚ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ ሳይመን ሞርዱ ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ከልማት ድጋፍ ወደ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረገ አጋርነት ለመቀየር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በኢንቨስትመንት እና ዘላቂ የስራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረትን የቁጥጥር ደንብን ተከትላ ቡናን ጨምሮ የተለያዩ ምርቶችን ማቅረብ በምትችልባቸው አማራጮች ላይ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር መስማማታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026