የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ባለፉት ዘጠኝ ወራት 374 የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ወደ ስራ ገብተዋል-ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

Apr 10, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦በበጀት አመቱ ዘጠኝ ወራት 374 ቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ወደ ስራ መግባታቸውን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።


ንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2017 የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው።


መድረኩ ቀጣናዊ ትስስር እና አለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለንግድ ዘርፍ እድገት በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።


የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥የበጀት አመቱ ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ከእቅድ በላይ የተፈጸመበት ነው።


ምቹ የንግድ ከባቢን ከመፍጠር አኳያ ከፍተኛ ስራ መሰራቱን ተከትሎ በበጀት አመቱ ዘጠኝ ከእቅድ በላይ ውጤት እንዲመዘገብ እንዳስቻለ አንስተዋል።


በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመፍታት የተከናወነው ስራ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ ቀደም የነበረውም የሲሚንቶ እጥረት መፍታት መቻሉን አንስተዋል።


ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና በተያያዘም የታሪፍ ማስማማት ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።


ከቅዳሜ እና እሁድ ገበያ አንጻርም ባለፉት ዘጠኝ ወራት 374 ተጨማሪ ገበያዎች ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል።


በጀት አመቱ ዘጠኝ ወራት ከወጭ ንግድ ከ4 ነጥብ 5 ቢልዮን ዶላር በላይ መገኘቱን ጠቅሰው፤በወጭ ንግድ የተገኘው ውጤት በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑን አመላክተዋል።


በበጀት አመቱ በተመዘገቡ ውጤቶች በማጠናከር በቀጣይ የላቀ ውጤት ለማምጣት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025