የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ4ሺህ 254 ኪሎ ግራም በላይ የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደርጓል

Apr 11, 2025

IDOPRESS

ጋምቤላ፤ ሚያዝያ 2/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ4ሺህ 254 ኪሎ ግራም በላይ የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ገለጸ።

ክንውኑ ከዕቅዱ በ2 ሺህ 404 ኪሎ ግራም ብልጫ እንዳለውም ተመላክቷል።

የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጁሉ ጊሎ ለኢዜአ እንደገለጹት እንደ ሀገር የብዝሃ ኢኮኖሚ አውታር ተብለው ተለይተው በልዩ ትኩረት እየተሰራባቸው ከሚገኙ ዘርፎች መካከል አንዱ የማዕድን ልማት መሆኑን ተናግረዋል።

ይህንንም ታሳቢ በማድረግ በክልሉ ያለውን ሰፊ የወርቅ ማዕድን ሀብት ከብክነት በመታደግ ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በባህላዊ፣ በልዩ አነስተኛና በወርቅ አምራች ኩባንያዎች ከ4ሺህ 254 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ተመርቶ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።

ለብሔራዊ ባንክ ገቢ የተደረገው የወርቅ ምርት ከእቅዱ በ2ሺህ 254 ኪሎ ግራም ብልጫ ያለው መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ይህም ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተግባራዊ በመደረጉና የተሻለ ሰላም በመኖሩ የተገኘ ውጤት መሆኑን ተባግረዋል።

እንዲሁም በቴክኖሎጂ የታገዘ የወርቅ ልማትና ከክልል እስከ ወረዳ የተጠናከረ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች በመደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዘርፉ ከተገኘው ስኬት በተጨማሪ ከስድስት ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፈጠሩን ጠቁመዋል።

በቀጣዮቹ ሶስት ወራትም የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር ለብሔራዊ ባንክ የሚቀርበውን የወርቅ ምርት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025