
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 2/2017 (ኢዜአ):-የትራንስፖርት ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የጭነት ትራንስፖርትን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር የሚያስችል የተቀናጀ የትራንስፖርት አስተዳደር (IFTMS) ሲስተም አስጀመረ።
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) ሲስተሙን መርቀው አስጀምረዋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትራንስፖርትና መሰረተ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ታለፍ ፍትህዓወቅ፣የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጊ ቦሩ እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የተቀናጀ የትራንስፖርት አስተዳደር (IFTMS) በኢትዮጵያ የጭነት ትራንስፖርት ለመቆጣጠር እና ለማስተዳደር የተዘጋጀ ሁሉን አቀፍ ዲጂታል ስርዓት መሆኑም ተገልጿል።
ሲስተሙ የተቀናጀና የተቀላጠፈ የሎጅስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም ተመላክቷል።
ከዚህም በተጨማሪ ዘርፉን የሚያዘምን ከመሆኑ በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን በመቅረፍ የህዝብን እርካታ የሚያሳድግ መሆኑ ተገልጿል።
ሲስተሙ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተለያየ ዘርፍ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑም እንዲሁ።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026