
መቀሌ፤ሚያዚያ 2/2017(ኢዜአ)፦በትግራይ ክልል ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲነቃቃና መንግስታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ሲሉ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ።
መጋቢት 30/2017 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬዚዳንትነት ርክክብ ሥነ-ሥርዓት መካሄዱ ይታወቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በሥነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የትግራይ ህዝብ ሰላምና መረጋጋት አግኝቶ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን መንግስት የተጠናከረ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት ሆነው የተሾሙት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ በቀጣይ ወራት ለማከናወን ያቀዷቸውን ሥራዎች አስመልክተው ዛሬ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
ሌተናል ጀነራል ታደሰ ከካቢኔያቸው ጋር ዛሬ ስብሰባ በማካሄድ በቀጣዩ ወራት ሊከናወኑ የሚገባቸው ሥራዎች ላይ መክረዋል።
በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ላይ እያንዳንዱ የመንግስት ተቋማት እቅዱን እንዲከልስና የቀጣይ በጀት ዓመት እቅድ እንዲያዘጋጅ አሳስበዋል።
የሁሉም ሥራዎች ማዕከል የሆነው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በተሟላ መንገድ ተግባራዊ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል።
የትግራይ ህዝብ ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ፤ የክልሉ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲነቃቃ የሚያደርግና መንግስታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ውጤት የሚያመጣ ስራ ይሰራል ነው ያሉት።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026