አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 4/2017(ኢዜአ)፦በማህበራዊ ሚዲያዎችና በኢንተርኔት የሚፈጸሙ የማጭበርበር እንቅስቃሴዎች እየበረከቱ ይገኛሉ።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከዚህ ጋር ተያይዞ እያጋጠሙ ያሉና ሊያጋጥሙ ይችላሉ ያላቸውን ስጋቶች መከላከል የሚያስችሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስቀምጧል።
የዲጂታል ማጭበርበሮችን ለመከላከል ልንወስዳቸው የሚገቡ የጥንቃቄ ርምጃዎችንም እንደሚከተለው አቅርቧል፦
ያልታወቁ አድራሻዎችን ወይም ሊንኮችን ከመክፈት በመቆጠብ፤ ከላይ ያሉትን ወይም ተመሳሳይ አድራሻዎች በመልዕክት፣ በማህበራዊ መገናኛ፣ ወይም በሌላ መንገድ ከደረስዎ ከመክፈት መቆጠብ በተለይ “እንኳን ደስ ያለህ! ገንዘብ አሸንፈሃል፣ ይህን አገናኝ ጫን” የሚል መልዕክት ከመጣ፣ ይህ ማጭበርበሪያ ሊሆን ስለሚችል መጠንቀቅ፤
የሞባይል እና የባንክ መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በመጠቀም፤ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን ከታመኑ ምንጮች (እንደ Google Play) ወይም አፕስቶር (app-store) ብቻ ያውርዱ።
የይለፍ-ቃልዎን ወይም የባንክ መለያዎችን ባልታወቁ ድረ-ገፆች ከማስገባት መቆጠብ፤
በዲጂታል ሚዲያዎች አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከቱ ሪፖርት በማድረግ፤ እንደዚህ አይነት መልዕክቶች ወይም አድራሻዎች ካዩ፣ ወዲያውኑ ለEthio-CERT በኢ-ሜይል ([email protected]) ወይም በስልክ (933) ያሳውቁ፤
በነፃ Wi-Fi ስንጠቀም በጥንቃቄ በመጠቀም፤ በካፌዎች፣ በሆቴሎች፣ ወይም በሌሎች የህዝብ ቦታዎች ያለውን ነፃ Wi-Fi ሲጠቀሙ፣ የግል መረጃዎችን አያስገቡ።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025