የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢንዱስትሪ ፓርኩ በተኪ ምርት፣በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በስራ እድል ፈጠራ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው

Apr 14, 2025

IDOPRESS

ዲላ፤ሚያዚያ 4/2017 (ኢዜአ) :-የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተኪ ምርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በስራ እድል ፈጠራ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የሲዳማ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ አራርሶ ገረመው (ዶ/ር) ተናገሩ።

የሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የፓርኩን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

የፓርኩ የቦርድ ሰብሳቢና የሲዳማ ክልል ልማትና ፕላን ቢሮ ሀላፊ አራርሶ ገረመው (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት በፓርኩ 8 ፋብሪካዎች በአቮካዶ ዘይት፣ በወተት፣ ማርና ቡና ማቀነባበር ወደ ስራ ገብተዋል።

በዚህም በተኪ ምርትና በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

በተለይ በግብርና ምርቶች አቅርቦት 136 ሺህ በላይ በህብረት ስራ የታቀፉ አርሶ አደሮች የገበያ ትስስር በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረጉን አንስተዋል።

ጉብኝቱ የፓርኩን ተሞክሮ ከማስፋት ባለፈ በምርት አቅርቦት ትስስር የተጀመረውን ግንኙነት ለማጠናከር ወሳኝ እንደሆነም ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደርና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፓርኩ በአካባቢው የገበያ ትስስር እየፈጠረ ነው ብለዋል።

ይህም ግብርናውን በማዘመን የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር የኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲነቃቃ እድል መፍጠሩን ማየታቸውን አንስተዋል።

በቀጣይ አርሶ አደሩ ምርታማነትን በማሳደግ በዘርፉ ያሉ እድሎችን እንዲጠቀም ከማገዝ ባለፈ በክልሉ በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ የአግሮ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ብርሃኑ፤ የመስክ ምልከታው በክልሉ መካከለኛ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ለማስገባት የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

በቀጣይ የግብዓትና የፋይናንስ አቅርቦት ውስንነቶችን በመቅረፍና በፓርኮቹ መካከል የተፈጠረውን ትስስር በማጠናከር የፓርኮቹን ውጤታማነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በጉብኝቱ የሁለቱ ክልሎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና አባላት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም አጋርና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025