የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በሐረሪ ክልል የኮሪደርና የቱሪስት መስህብ ስፍራ ልማቶች የጎብኚዎችን ቁጥር እንዲጨምር አስችሏል

Apr 15, 2025

IDOPRESS

ሐረር፤ ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል የኮሪደርና የቱሪስት መስህብ ልማቶች የጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ቅርስ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የክልሉን የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ከጎበኙ ከ130ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ከ136 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱም ተገልጿል።


የቢሮው ሃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ እንደገለጹት ቢሮው የክልሉ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችን በማስተዋወቅና በማልማት የጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል።

የቱሪስት መስህቦች ልማት ከተካሄደባችው መካከልም የዓለም አቀፍ ቅርስ በሆነው ጀጎልን ጨምሮ ሌሎች የኮሪደርና የመስህብ ስፍራዎችን የመንከባከብ፣ የመጠበቅና የማስዋብ እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎች ለጎብኚዎቹ ቁጥር መጨመር ጉልህ ሚና ማበርከታቸውን አመልክተዋል።

እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የሸዋል ኢድ በዓል አከባበርም ለጎብኚዎች ቁጥር መጨመር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።


በሐረሪ ክልል በቱሪስቶች ከሚጎበኙት ቅርሶች መካከል የዓለም ቅርስ የሆነው የጀጎል ግንብ፣ በውስጡ የሚገኙ ጥንታዊ መኖሪያ ቤቶችና አምስቱ የጀጎል ግንብ መግቢያ በሮች ይገኙበታል።

በተጨማሪም ባህላዊ የዕደ ጥበብ ውጤቶች፣ የፈረንሳዊው ባለቅኔ አርተር ራንቦ መኖሪያ ቤት፣ የሐረሪ ብሔረሰብ ሙዚየሞች፣ አድባራት፣ የጅብ ምገባ ትርኢትና ሌሎችም በቱሪስቶች የሚገበኙ ጥንታዊ፣ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ የመስህብ ስፍራዎች ናቸው።

በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የክልሉን የመስህብ ስፍራዎችን 7ሺህ 877 የውጭ ቱሪስቶች ጎብኝተዋል ያሉት ሃላፊው፤ ይህም ከዓምናው ጋር ሲነጻጸር በ31 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው የገለጹት።

በተጨማሪም ከ123ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በክልሉ የሚገኙ የመስህብ ስፍራዎችን መጎብኘታቸውን ገልፀው፤ ይህም ከዓምናው በ7 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አክለዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን የተከናወነው የኮሪደር ልማት ግንባታና የማስዋብ ሥራዎቹ ከተማውን ለቱሪስቶች ምቹና ውብ እንዲሆን ማስቻላቸውንም አቶ ተወለዳ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025