
አዲስ አበባ ፤ሚያዚያ 6/2017(ኢዜአ):- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ አበረታች ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሸ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የአስተዳደር ዘርፍ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ርዕሰ መስተዳድር ነጋሸ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል።

የክልሉ ርዕሰ መስተደድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ርኢ/ር) በክልሉ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በሀብት ብክነት፣ ከልማት ሥራዎች ውጤታማነት ችግር ጋር የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በተቀናጀ መልኩ መፍታት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በክልሉ ሰላም እና ፀጥታ፣ተቋማት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
ወንጀል፣ሙስና እና ብልሹ አሰራር እንዲሁም ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን መከላከል የተለየ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።
እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ፤ ከህዝቡ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል የሚባክን የመንግስት በጀት ማዳንና የህግን የማስከበር ሥራ ማከናወን ይገባል።
የባህል ፍርድ ቤቶች ማጠናከር እና የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራ ማፋጠን እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።
በሌላ በኩል በክልሉ በመንግሥት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን በቴክኖሎጂ መደገፍ እና ህዝብን ከማገልገል አንጻር ጠንካራ የአሰራር ሥርዓት ሊዘረጋ ይገባልም ነው ያሉት።
በክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ወቅታዊ እና ሚዛናዊነቱን የጠበቀ መረጃዎችን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች መጠናከር እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በክልሉ የመንግሥት የልማት ሥራዎችን የሚያደናቅፉ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በተቀናጀ መልኩ መፍታት እንደሚጠበቅም መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026