
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2017(ኢዜአ)፦ በየዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን በላቀ ውጤት ለማስቀጠል በጊዜ የለንም መንፈስ በትጋት መስራት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና የዘርፎች ዕቅድ አፈጻጸምን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ከፌዴራል ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር መገምገም ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ በ100 ቀናት የትኩረት ማዕከል የሆኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶች፣ የታዩ ክፍተቶች እና የትኩረት አቅጣጫዎች ከተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ እንደሚታዩ ይጠበቃል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ እና በተለያዩ መስኮች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
በየዘርፉ የተሰሩ ስራዎችን በአግባቡ መለካት፣ ማቅረብ እንዲሁም ለሌላው ማስረዳት እንደሚገባ ገልጸው፤ አሁንም አመራሩ በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።
ሰራተኛውን በአግባቡ የማይመራ፣ የማይመዝን እና የማይከታተል መኖሩንና በጥቂት ታታሪ ሰራተኞችና ኃላፊዎች ተቋማት የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ እንደሚስተዋል ገልጸው፤ ይህንን መፈተሽ እና ማስተካከል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከታሰበው በላይ የተሳኩ ድሎች መመዝገባቸውን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሁንም ትኩረት የሚፈልጉ አካባቢዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
አገራዊና ዓለም አቀፋዊ አውድን በመገንዘብ እየተገኙ ያሉ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸው የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ከዚህ በላይ መሮጥ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ እና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርምን መፈጸም ውዴታ ሳይሆን ግዴታ መሆኑንም ተናግረዋል።
አገልግሎት አሰጣጥ ሁሉንም ሊያሳስብ የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በጠንካራ አመራር እና ሰራተኛ የታጀበ አገልግሎት አሰጣጥ መኖር እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ከተገኙ ውጤቶች በላይ ለማሳካት ሁሉም በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026