አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2017 (ኢዜአ)፦ለ2017/18 የምርት ዘመን ከሚያስፈልገው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን 10 ሚሊዮን ኩንታል የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ።
የ2017 በጀት ዓመት የሦስተኛው ሩብ ዓመት የ100 ቀን አፈጻጸም እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፥ ለግብርና እና ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚውሉ የካፒታል እቃዎችን ጨምሮ የገቢ ምርቶች በከፍተኛ መጠን ማደጋቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እየተገበረች በምትገኘው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች በተመሳሳይ ከፍተኛ ለውጥ ማሳየታቸውን ጠቅሰዋል።
ሚኒስቴሩ የኢኮኖሚው እድገት ይዞ የመጣውን የመጫን አቅምን የመጨመር ፍላጎት ለመሸከም የሚያስችል ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዚህም ያለውን አቅም አሟጦ በመጠቀም በዘርፉ የአገልግሎት ቅልጥፍናን ማሳደግ መቻሉን ገልጸው፤የባቡር እና አሽከርካሪዎች የመፈጸም አቅም በማሳደግ በተከናወኑ ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን በማሳያነት አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በሎጂስቲክስ ዘርፍ እንዲሁም በወጪ እና ገቢ ንግድ ምርቶች ላይ ለተገኙ አመርቂ ስኬቶች ጉልህ ሚና መጫወታቸውን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፉ ስኬቶች ማሳያ የሆነውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ በጊዜው ለማድረስ በስፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በዘንድሮው የምርት ዘመን እስካሁን 10 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን አመልክተዋል።
ይህም ከታቀደው 24 ሚሊዮን ኩንታል አንጻር 42 በመቶ የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙንና ቀሪውን በተሳካ ሁኔታ ለማምጣት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ዘርፍም በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ብቻ ሲከናወን የነበረውን ስራ ለ6 የግል ኩባንያዎች ፈቃድ በመስጠት የጭነት እና የሎጂስቲክስ አቅምን ለማሻሻል መቻሉንም ነው ያብራሩት።
በአጠቃላይ የሎጂስቲክስ አፈጻጸሙ ትልቅ መሻሻል ማሳየቱን አመልክተዋል።
አሰራርን ለማዘመን የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ተደራሽነት እና የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎትን ማስፋት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር እና አቅምን ማጎልበት በቀሪው የበጀት ዓመት ወራት የሚከናወኑ ዋንኛ ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025