የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች በብዛትና በዓይነት እየቀረቡ ነው

Apr 18, 2025

IDOPRESS

ደብረ ብርሃን፣ደሴና መተማ፤ ሚያዚያ 9/2017 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በደብረ ብርሃን፣ በደሴና በመተማ ከተሞች ለትንሳኤ በዓል የሚያስፈልጉ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች በብዛትና በዓይነት በማቅረብ የገበያ ማረጋጋት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የከተሞቹ ነዋሪዎችም በመምሪያዎቹ ለትንሳኤ በዓል የሚሆኑ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች እየቀረቡ መሆኑን ገልፀው እሰከ በዓሉ መዳረሻ ቀናት እንደ አቅማቸው እንደሚሸምቱም ተናግረዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ንግድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘውገ ንጉሴ ለኢዜአ እንደገለጹት አርሶ አደሩ በየአካባቢው በተቋቋሙ የግብይት ማእከላት ምርቱን በስፋትና በጥራት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ እያቀረበ ነው።

የበዓል ገበያውን ለማረጋጋትም መስተዳድሩ 184 ሚሊዮን ብር ለሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በተዘዋዋሪ ብድር በማቅረብ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ቀድሞ መስራቱን ገልጸዋል።

በቂ ምርት ለማቅረብም ከአምራች ኢንተርፕራይዞች ጋር በማስተሳሰር 1 ሺህ 500 ኩንታል ቀይ ሽንኩርት በማቅረብ አንደ ኪሎው እስከ 40 ብር እየተሸጠ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም 650 የቀንድ ከብት፣ ሰባት ሺህ የበግና ፍየል ሙክት፣ 45 ሺህ የስጋ ዶሮና ከ498 ሺህ በላይ እንቁላል በትስስሩ እየቀረበ መሆኑን አስረድተዋል።

ከኢንዱስትሪ ምርቶችም 540 ኩንታል ስኳር፣ 400 ኩንታል የዳቦ ዱቄትና 100 ሺህ ሊትር ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ማቅረብ መቻሉን አረጋግጠዋል።

በአጎለላጠራ ወረዳ ጨኪ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ዘነበ አሰፋ እንዳሉት ያደለቡትን ሰንጋ በተመጣጣኝ ዋጋ ለመሸጥ ወደ ገበያ መውጣታቸውን ተናግረዋል።

በተያያዘም በደሴ ከተማ አስተዳደር ለትንሳኤ በዓል የሚያስፈልጉ ምርቶችን በማቅረብ የገበያ ማረጋጋት ስራ መሰራቱን የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አቶ ኃላፊ ዮናስ እንዳለ ተናግረዋል።

በዚህም ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ዘይት፣ እንቁላል፣ ዶሮና ሌሎችም ለበዓል የሚያስፈልጉ ምርቶች በመቅረባቸው ህብረተሰቡ ተረጋግቶ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት ይችላል ብለዋል።

በተለይም ከ30 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች 126 ሺህ ሊትር ዘይትና ዱቄት በዱቤ ጭምር ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል።

የደሴ ከተማዋ ነዋሪ የሆነው ወጣት መካሽ ያየውሰው በበኩሉ፥ ለትንሳኤ በዓል በተቋቋመው የገበያ ማእከል ከ15 ሺህ በላይ እንቁላል ለሸማቹ ማህበረሰብ ማቅረቡን ተናግሯል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር የበዓል ገበያውን ለማረጋጋት 20 ሚሊዮን ብር በተዘዋዋሪ ብድር በመመደብ ገበያው እንዲረጋጋ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑም ተገልጿል።

በሌላ በኩል በገንዳ ውሃ ከተማ ለመጪው ትንሳዔ በዓል የእርድ እንስሳት በቂ አቅርቦት መኖሩን የገለጹት ደግሞ በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንዳ ውኃና ኮኪት ከተማ ነዋሪዎች ናቸው።

የገንዳውሃ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ደሳለኝ አባቡ በከተማው ለበዓሉ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ውጤቶች በበቂ ሁኔታ እየቀረበ መሆኑን ገልፀዋል።

ሌላኛው በመተማ ወረዳ ኮኪት ከተማ ነዋሪና በስጋ ቤት ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ ሲሳይ ደሴ በበኩላቸው፥ በዚህ ዓመት የእርድ በሬ ከ80 ሺህ ብር ጀምሮ በመሸጥ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን እንስሳት ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ተወካይ ኃላፊ አቶ ሙሀመድ ሁሴን እንደገለጹት፥ ዞኑ ሰፊ የእንስሳት ሀብትና መኖ ያለው በመሆኑ ለትንሳዔ በዓል በቂ የቁም እንስሳት ማቅረብ ተችሏል።

እስካሁንም ከ35 ሺህ በላይ የዳልጋ ከብት፣ ከ79ሺህ በላይ የፍየልና ሌሎች ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች መቅረባቸውንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025