
ሐረር፣ሚያዚያ 14/2017(ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ለውጦች መመዝገባቸው ተገለፀ።
በክልሉ እየተካሄደ በሚገኘው የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የክልሉ የግብርና ልማት ቢሮና የክልሉ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ሪፖርቶች ቀርበዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተደድር እና የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ዑመር በወቅቱ እንዳሉት፤ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት በገጠርና በከተማ የሚገኘውን ህብረተሰብ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እያሸጋገሩ ይገኛሉ።
በሌማት ትሩፋት፣በከተማ ግብርና፣በመስኖ ልማት፣በመኸርና በበልግ ወራት የተሰሩ ስራዎች በሁለት ወረዳዎች የሚገኙ ከ1 ሺህ 800 በላይ ቤተሰቦችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እንዲሸጋገሩ ማድረጉን አንስተዋል።
በዘንድሮ በጋ ወራት 4 ሺህ 600 ሄክታር መሬትን በመስኖ በማልማት ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአዝርዕት፣ የፍራፍሬና አትክልት ምርቶች ሊሰበሰብ መቻሉን ገልጸዋል።
በተለይ በገጠርና በከተማ በዓመት ሶስት ጊዜ የማምረት ባህልን ለማጎልበት የተሰሩ ህዝባዊ ንቅናቄዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እያመጡ መሆኑን አመልክተዋል።
ለአብነትም ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሽላን በመስኖ ማምረት እንደሚቻል በሰርቶ ማሳያ በማሳየት በክልሉ ገጠር አካባቢ የሚኖረው ህብረተሰብ ስራውን ወደ ተግባር ለመቀየር ዝግጁ እንዲሆን መደረጉንም አስረድተዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተሰሩ ስራዎች ምርትና ምርታማነት እንዲጨምርና ከተረጂነት መላቀቅ እንደሚቻል ያሳዩ ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገበባቸው መሆናቸውን ወይዘሮ ሮዛ ተናግረዋል።
በበጋ ወራት የተመረቱ የቲማቲም፣ የቃሪያ እና የሽንኩርት ምርቶች ለቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ቀርበው ዋጋ በማረጋጋት ረገድ ዓይነተኛ ሚና መጫወታቸውን ገልፀዋል።
በቀሪ በጀት ወራት የተገኙ ውጤቶችን ከማጠናከር በተጨማሪ ለቀጣይ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ የችግኝ ዝግጅት ስራን የማጠናቀቅ እና የማዳበሪያ አቅርቦትን የማፋጠን ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
የክልሉ የባህል፣ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ፤ ከ130 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ አገራት ቱሪስቶች የክልሉን የቱሪዝም ሃብቶች መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
ከእነዚህ መካከል 123 ሺህ የሀገር ውስጥ ሲሆኑ ቀሪዎቹ የተለያዩ አገራት ቱሪስቶች መሆናቸውን አንስተው በዚህም 14 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።
ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ30 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸው በክልሉ ቱሪዝም ጥሩ የሃብት ምንጭ እየሆነ መምጣቱንም ገልፀዋል።
በተለይም የኮሪደር ልማት ክንውኑ ከተማዋን ውብና ለቱሪስቶች ምቹ ያደረጋት መሆኑን ጠቅሰው ታሪካዊ መስህቦችና ሌሎች የክልሉ እምቅ የቱሪዝም ሃብቶች መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026