የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የቡና ጥራትን በማሻሻል የዘርፉን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

Apr 24, 2025

IDOPRESS

ጅማ፣ሚያዝያ15/2017(ኢዜአ)፡- የቡና ጥራትን በማሻሻል ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግና የአምራቹን ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

አርሶአደር ተኮር ጥራቱን የጠበቀ የስፔሻሊቲ ቡና አዘገጃጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በጅማ ከተማ እየተሰጠ ነው።

የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ታጋይ ኑሩ እንደገለጹት የቡና ጥራትና ደረጃ በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን የገቢ መጠን ለማሳደግና የቡና አምራቹን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ።

በቡና ጥራት የማይደራደር አርሶአደር ለመፍጠር የቡና ጥራት ንቅናቄ ሲደረግ መቆየቱን ጠቅሰዋል ።

“በሁሉም የቡና አምራች አካባቢዎች የቡና ጥራትና ጣእም ተቀባይነትን የሚያረጋግጡ ስራዎችን መተግበር ያስፈልጋል” ብለዋል።

“ጥራቱን የጠበቀ ቡናን ለማዘጋጀት ከተለመደው የተለየ አሰራር መተግበርና በትኩረት መከታተል ያስፈልጋል” ያሉት አቶ ታጋይ ጥራት በገበያው ላይ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አስታውቀዋል ።

የጅማ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አወል ከሊል በበኩላቸው “የዞኑን የቡና ምርት ጥራት ደረጃን ለማሻሻል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው” ብለዋል።

በዞኑ የሚመረተው ቡና በማእከላዊና በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን የእፔሻሊቲ ቡና ጥራት ላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰራ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሚተገበር መሆኑን አመልክተዋል ።

ቡና አምራች አርሶ አደሮችን፣ ነጋዴዎችና ባለሞያዎችን እንዲሁም የማጠቢያና መፈልፈያ ኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን ያሳተፈ ውይይት መደረጉን አስታውቀዋል ።

“ስልጠናው በቡና ጥራት የታዩ ጉድለቶችን ለማረምና ጥራቱ ላይ ትኩረት እንድናደርግ የሚያግዝ ነው “ ያሉት ደግሞ ቡና አምራች አርሶአደር ሙስጠፋ መሀመድ ናቸው ።

ሌላው አርሶ አደር ሙስጠፋ አባ ቀኖ በበኩላቸው “ቡና በምርት ስብሰባ ወቅት፣ በመጋዘን ቆይታውና በማጓጓዝ ወቅት ሊበላሽ የሚችል በመሆኑ የግንዛቤ ስልጠናው በስፋት መሰጠት አለበት” ብለዋል።

በስልጠናው ላይ ከኦሮሚያ ክልል ከጅማ፣ ኢሉ አባቦርና ቡኖ በደሌ ዞኖች እንዲሁም ከደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከካፋና ከቤንች ሸኮ ዞኖች የተውጣጡ አምራቾችና ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025