
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2017(ኢዜአ)፦ ወጥነት ያለው ጥራት በሁሉም የግብርና ምርቶች ላይ ልናሳይ ይገባል ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ምርትና ግብዓት ጥራት ምርመራ ማዕከል አክሪዲቴሽን ትውውቅና የሰርቲፍኬት ርክክብ ፕሮግራም ተካሂዷል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የምግብ ዋስትናና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፣ ገቢ ምርቶችን መተካት እና ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚውሉ በብዛትና በጥራት ማምረት ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን በብዛት ከማምረት ጎን ለጎን ጥራቱን ማረጋገጥ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ቀደም ሲል የነበረው የግብርና ፖሊሲ ማምረት ላይ እንጂ ጥራትን ታሳቢ ያላደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ወጥነት ያለው ጥራት በሁሉም የግብርና ምርቶች ላይ ልናሳይ ይገባል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ያለው የእንስሳት ምርትና ግብዓት ጥራት ምርመራ የእንስሳት ምርትና ግብዓት ጤንነት የሚያረጋገጥ አንዱ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ ተሞክሮ በእጽዋትና በሁሉም ዘርፍ በቀጣይነት ማስፋፋት ይገባል በማለትም አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ፤ ባለስልጣኑ የግብርና ምርትና ግብዓት ጥራትና ደህንነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ የጥራት መስፈርቶችን፣ ህጋዊ ማዕቀፎችንና የቴክኖሎጂ አሰራሮችን በመዘርጋት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
በባለስልጣኑ ደረጃቸውን የጠበቁ የእንስሳት ምርትና ግብዓት ጥራት ደህንነት ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ 13 የምርመራ ላቦራቶሪዎች በሶስተኛ ወገን እውቅና ማግኘቱን ገልጸዋል።
ይህም የግብርና ምርትና ግብዓት ቁጥጥር ደረጃን የሚያሳድግ መሆኑን በመግለጽ፡፡
የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ቦንሳ ባይሳ በበኩላቸው፤ አክሪዲቴሽን ተቋማት የተሻለ አሰራር ሥርዓት እንዲከተሉ፣ ሂደታቸውን ያለማቋረጥ እንዲያሻሽሉ የሚያበረታታና ተወዳዳሪነታቸውን በሚጨምር መልኩ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በባለስልጣኑ የእንስሳት ምርትና ግብዓት ጥራት ምርመራ ማዕከል ኃላፊ ዶክተር በላቸው ተፈራ፤ በበኩላቸው ማዕከሉ ባለፉት አስር ዓመታት የዓለም አቀፍ ደረጃውን የተከተለ አደረጃጀት፣ ኬሚካል አጠቃቀምና ምርመራን ተግባራዊ ማድረጉ ለዚህ ውጤት እንዳበቃው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የሚሰጣቸው 66 አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ማድረጉና ተገልጋዮች ወደ ተቋሙ መምጣት ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ቦታ ሆነው በዲጂታል አማካኝነት አገልግሎቱን እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ለአብነትም እንደ አበባ፣ ቡና፣ ስጋ፣ ተረፈ ስጋ፣ የቁም እንስሳት፣ የእንስሳት መኖ፣ የእንስሳት መድኃኒት ያሉ የወጪና ገቢ ምርቶች ላይ ፍተሻ በማድረግ የመግቢያና መውጫ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተመላክቷል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026