አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2017(ኢዜአ)፦ የ2017 ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል።
የሩጫ ውድድሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ውድድሩም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ 4ኛ ዓመት ዝግጅትን አስመልክቶ የተሰናዳ መሆኑ ተገልጿል።
በዝግጅቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።
አቶ መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት፤ ውድድሩ የሀገራችንን ምርት ለአለም ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ብለዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው፤ ባለፉት የለውጥ አመታት በተሰሩ ስራዎች ስፖርት ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው ተደርጓል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ ከውጪ ይገቡ የነበሩ የስፖርት ልብሶች ጥራታቸውን ጠብቀው በሀገር ውስጥ መመረት መጀመራቸውን በመግለጽ።
ውድድሩ ባለሃብቶች በስፖርቱ ዘርፍ መዋለ ንዋያቸውን ፈሰስ በማድረግ አስፈላጊ ምርቶችን በማምረት ድጋፍ እንዲያደርጉ እና በሀገር ውስጥ አምራቾች የተመረቱ የስፖርት አልባሳትን ለማስተዋወቅ እንዲሁም አስፈላጊውን የገበያ ትስስር ለመፍጠር መዘጋጀቱ ተገልጿል።
መነሻና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ባደረገው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በሁለቱም ፆታዎች በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የ300ሺህ፣ የ200ሺህ እና የ100ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትላቸው ይሆናል።
በክለብ ደረጃ በሁለቱም ፆታዎች ተወዳዳሪዎቻቸውን ለሚያሳትፉ ክለቦች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለሚወጡም እንዲሁ ሽልማት ተዘጋጅቷል።
በውድድሩ የአምራች ኢንዱስትሪ ተዋናዮች፣ አጋር ድርጅቶች፣ ከ34 በላይ የአትሌቲክስ ክለቦችና መላው የአትሌቲክሱ ቤተሰቦች በአጠቃላይ ከ14 ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025