አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2017(ኢዜአ)፦ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የዓለም ሀገራት የርቀት ስራ የሚያገኙበትን ዕድል እየፈጠረ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዜጎች በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልጸግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሰረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው ለማስቻል የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያን ኮደርስ ስልጠና በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ማስጀመራቸው ይታወቃል፡፡
በዚህም በርካታ ወጣቶች አቅማቸውን ለማሳደግ፣ ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ዘመኑን የዋጀ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለመሆን ስልጠናውን በኦን ላይን እየተከታተሉ ናቸው፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ለወጣቶች ሥራ ፈጠራ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር እምቅ አቅም አለ፡፡
ይህን አቅም በእውቀትና በክህሎት እንዲመራ በማድረግ ወጣቶች ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ አቅም ታጥቀው ወደ ስራ እንዲገቡ ማስቻል ደግሞ ተጠባቂ እንደሆነ ገልጸዋል።
በዚህም መንግሥት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ተቋማትን በብቁ አሰልጣኞችና በመሰረተ ልማት በማበልጸግ ለወጣቶች የሥራ እድል እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ተቋማት በዓመት በአማካኝ እስከ ሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎችን እንደሚያሰለጥኑ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴሩ በቢዝነስ ልማት መርሃ ግብሩ ወጣቶችን በሥነ ልቦናና ቴክኒክ እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸው፤ በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ለሦስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የውጭ የሥራ ስምሪት ስምምነት መፈራረሟን ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ለ344ሺህ ዜጎች የውጭ የሥራ እድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
የ21ኛ ክፍለ ዘመን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚጠይቀውን ሥርዓተ ትምህርት በመቅረፅ ወጣቶች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲኖራቸው እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያን ኮደርስ ስልጠና የወጣቶችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም በማላቅ ከተለያዩ ሀገራት የርቀት ሥራ ዕድል እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል፡፡
በስልጠናው የሚሰጡ ኮርሶች ዓለም አቀፍ እውቅና የሚያሰጡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ 45ሺህ ዜጎች በተለያዩ ሀገራት የርቀት ሥራ እንዲያገኙ ማገዙን ተናግረዋል፡፡
ከተለያዩ ሀገራት ኩባንያዎች ተጨማሪ ጥያቄ እየቀረበ መሆኑን ጠቅሰው፤ ወጣቶች ሥራው የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ አቅም ገንብተው ወደ ሥራ መግባት ይችላሉ ሲሉም ገልጸዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025