ደሴ፤ ሚያዝያ 23/2017(ኢዜአ)፦ በየዘርፉ ያሉ አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶች የሀገርን እድገትና ብልጽግና እውን ለማድረግ ትልቅ አቅም መሆናቸውን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ አህመዲን መሀመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ከሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኮምቦልቻ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 9ኛው የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር እና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ትርዒት እና የደረጃ ሽግግር ሳምንት ተጠናቋል፡፡
በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ አህመዲን መሀመድ(ዶ/ር)፤ በሁሉም ዘርፎች የሚስተዋሉ አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶች የሀገርን እድገትና ብልጽግና እውን ለማድረግ ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሀገርን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ አዳዲስ ፈጠራዎችን ማበርከት፣ የዲጅታል ክንውንና ዘመናዊ አሰራሮችን ማስፋት ይገባል ብለዋል።
በዚህ ረገድ በተለይም የወጣቶችን ፈጠራ ለማሳደግ በመንግስት ድጋፍና ማበረታቻ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የክልሉ መንግስት ተገቢውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አንስተው፤ ሥራና ስልጠና ቢሮ ባካሄደው የፈጠራ፣ የክህሎትና የቴክኖሎጂ ውድድር ተስፋ ሰጭ ውጤቶች በማየታችን ተደስተናል ብለዋል።
በወጣቶች የቀረቡት የፈጠራ ስራዎች በተለይም ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ አቅም የሚሆኑና የአርሶ አደሮችን ድካም የሚቀንሱ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ሥራ እና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የፈጠራ ሥራዎችን በመደገፍና በማበረታታት ለብዙዎች ተደራሽ እንዲሆኑና በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል ብለዋል።
በተለይ የአርሶ አደሮችን የምርት ጥራት የሚጠብቁ፣ ብክነትን የሚያስቀሩ፣ ጊዜና ጉልበትን የሚቆጥቡ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች ያሏቸው ወጣቶችን መደገፍና ማበረታታት እንደሚገባ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025