የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የፈጠራና የቴክኖሎጂ ግኝቶች ፈጥነው ወደ ምርትና አገልግሎት እንዲገቡ በትብብር መስራት ይገባል - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

May 6, 2025

IDOPRESS

አዳማ፤ ሚያዚያ 23/2017(ኢዜአ)፡- የፈጠራና የቴክኖሎጂ ግኝቶች ፈጥነው ወደ ምርት እና አገልግሎት እንዲገቡ በትብብር መስራት እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ገለጹ።

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ላለፉት አራት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የፈጠራ ውድድርና አውደ ርዕይ ተጠናቋል።


የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ እንደገለፁት የክህሎት፣ ፈጠራና ቴክኖሎጂ ውድድርና አውደ ርዕይ እንደሀገር ከድህነት ለመውጣት የሚደረገውን ሂደት የሚደግፍ ነው።

በመሆኑም ክህሎት፣ ልዩ ተሰጥኦና የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ወጣቶች የፈጠራ ውጤቶችን ወደ ምርት እና አገልግሎት ማስገባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በዚህ ሂደት ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ባለፈ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የቴክኖሎጂና የፈጠራ ውጤቶች ለተግባር ሥራ እንዲውሉ የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት።

በክልል ደረጃ በተካሄደው ውድድር የተሻለ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ወጣቶች ውጤታማ ሥራ ማቅረባቸውንም ገልጸዋል።


የኦሮሚያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ኤባ ገርባ በበኩላቸው በክልሉ በክህሎት፣ በቴክኖሎጂና በፈጠራ የበቃ ተወዳዳሪ የሰው ሃይል ማፍራት ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በተለይም ኮሌጆች ቴክኖሎጂን በመቅዳት፣ በማላመድና በማበልፀግ ለልማት እንዲውሉ ማድረግ ላይ የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸዋል።

ሰሞኑን በአዳማ ከተማ በ22 ክላስተር ሲካሄድ የቆየው ውድድርና አውደ ርዕይ በቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ክህሎት የበቃ ትውልድ ማፍራትን ዓላማ ማድረጉንም አስታውሰዋል።

በውድድሩ የፕላስቲክ ምርቶችን መልሶ መጠቀምና ማጽዳት፣ በግብርና፣ በትራንስፖርት እንዲሁም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት የሚያስችሉ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውጤቶች መቅረባቸውን ጠቅሰዋል።

እነዚሁ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በተሻለ ደረጃ ለማበልፀግና በስፋት በማምረት ወደ ገበያ እንዲገቡ የክልሉ መንግሥት ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለዚህም በቢሾፍቱ፣ ነቀምት፣ አዳማ እና ሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከላት የተመረጡ የፈጠራ ውጤቶችን በስፋት አምርተው ለገበያ እንዲያቀርቡ እየተሰራ መሆኑን አውስተዋል።


በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያ፣ የዋንጫ፣ የታብሌትና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025