ሐዋሳ፤ሚያዚያ 24/2017 (ኢዜአ)፦በቴክኖሎጂና ምህንድስና ዘርፎች የምርምር ስራዎችን ለሀገር እድገት ለማዋል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡
ለሁለት ቀናት የሚካሄደው 7ኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በዛሬው እለት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መካሄድ ጀምሯል።
የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ታፈሰ ማቲዎስ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥በምህንድስናና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚደረጉ የምርምር ስራዎችን በማጠናከር እንደሃገር የተያዙ የልማት ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በተለይም በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት ዩኒቨርሲቲው አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችንና ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማካሄድ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሚዘጋጀው የምርምር ኮንፈረንስም በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ተቀናጅቶ በመፍታት ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ውጤቶች የሚገኝበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ዩኒቨርሲቲው ከሀዋሳና ከይርጋለም ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር በመቀናጀት የሚወገዱ ተፈረ ምርቶችን መልሶ ለመጠቀም የሚያስችሉ ችግር ፈቺ ምርምሮችን አድርጓል ብለዋል፡፡
በቴክኖሎጂና ምህንድስና ዘርፎች የምርምር ስራዎችን ለሀገር እድገት ለማዋል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ምህረት ደናንቶ (ዶ/ር) በምርምር ኮንፈረንሱ በፈጠራ ላይ ያተኮሩ 32 ጥናታዊ የምርምር ስራዎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው መሆኑን ጠቁመዋል።
"ኢትዮጵያን በምህንድስናና ቴክኖሎጂ ፈጠራ መድረስ" በሚል መሪ ሃሳብ ከተዘጋጀው መድረግ የሚገኙ ውጤችም የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በኢንስቲትዩቱ የተሰሩ የምርምር ስራዎችን ወደ ፈጠራ በመቀየር ከውጭ የሚገቡ ማሽነሪዎችን በሃገር ውስጥ የመተካት፣ሰው ሰራሽ አካል የማምረትና ከወዳደቁ የፕላስቲክ ውጤቶች የተለያዩ ስራዎች የተሰሩ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
በተለይም በውሃ ማእድንና ኢነርጂ ዘርፍ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ዩኒቨርሲቲው ጥናትን መሰረት ያደረገ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
በመድረኩ የተገኙት የሲዳማ ክልል ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ከበደ ጋኖሌ፤ በክልሉ በማእድን ዘርፍ ያሉ አቅሞችን የመለየት፣በመስኖና በመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ላይ በተሰሩ በጥናት የተደገፉ ስራዎች ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን የምርምር ስራዎቻቸውን አቅርበው ውይይት እንደተደረገባቸውም ታውቋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025