አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 27/2017(ኢዜአ)፦የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪን በተሟላ አቅም ወደልማት ለማስገባት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ከተሞች ልማት ክላስተር አስተባባሪና ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የአማራ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ውስጥ ከገቡ አልሚ ባለሀብቶች ጋር የውይይት መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በመድረኩ የተገኙት ዶክተር አሕመዲን መሐመድ ግብዓትና የኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ ምርታማነት አቅም መሰረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል።
በዚህም በ260 ሔክታር መሬት ላይ በለማው የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሰባት የገጠር ሽግግር ማዕከላትን ጨምሮ ምቹ የመሠረተ ልማት መዘርጋቱን ገልጸዋል።
በቀጣይም የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪን በተሟላ አቅም ወደ ልማት በማስገባት ለአልሚ ባለሃብቶች ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
መድረኩ የቡሬ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበትን ሁኔታ ለመረዳት፣ ለመማማርና ልምድ ለመቀያየር እንዲሁም በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍትሔ ለመስጠት የሚረዳ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማትና አቅም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አድማሱ ይፍሩ፥ መንግስት የቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ለኢንዱስትሪ ምርታማነት አቅም የሆኑ ፓርኮች መገንባታቸውን ተናግረዋል።
በዚህም በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ የሚስተዋሉትን የኃይል አቅርቦትና ተያያዥ ችግሮች መፍትሔ በመስጠት ወደተሟላ የምርታማነት አቅም ለማስገባት ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
ባለሀብቶችም ከሀይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚያነሱት ጥያቄ በቀጣይ የሚቀረፍ መሆኑን በመገንዘብ በሙሉ አቅም ወደስራ ለመግባት ዝግጁ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብርሃኑ ጣምያለው፥ በክልሉ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ አቅም የሚሆን ሰፊ የተፈጥሮ ሃብት መኖሩን ገልጸዋል።
በዚህም ክልሉን የኢንዱስትሪ ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በቀጣይም የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ በሌሎች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የተሰማሩ አልሚዎችን ወደተማላ የማምረት አቅም ለማሸጋገር ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ አንስተዋል።
በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ አልሚ ምግብና የምግብ ዘይት ጨምሮ የግብርና ምርት ውጤቶችን በማቀነባበር ለገበያ እያቀረበ እንደሚገኝም ተገልጿል።
በምክክር መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አመራሮች፣በቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዳስትሪ በኢንቨስትመንት የገቡ ባለሃብቶችና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።
በፓርኩ የገጠር ሽግግር ማዕከላት ወደስራ የገቡ አልሚዎችና በግንባታ ላይ ያሉትን አሁናዊ ሁኔታ የሚያሳይ መነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ምክክር እየተካሄደበት ይገኛል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025