ባህር ዳር፤ሚያዚያ 27/2017(ኢዜአ)፦በባህርዳር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን 17 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የከተማ ከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።
አቶ ጎሹ እንዳላማው እንደገለጹት፥ ባህር ዳር ከተማ ተመራጭ የቱሪስትና የኢንቨስትመንት ማዕከል እንድትሆን ለመሰረተ ልማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል።
በዚህም በከተማዋ በተለያየ ጊዜ ተጀምረው በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ 22 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የአስፋልት መንገዶች እንዳሉ ተናግረዋል።
መንገዶቹም ከ20 እስከ 40 ሜትር ስፋት ያላቸውና የእግረኛ፣የሳይክል፣ የአረንጓዴ ልማትና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ያሟሉ ናቸው ብለዋል።
በግንባታ ሂደት ውስጥ ካሉትም 17 ኪሎ ሜትር የሚሆነውን የአስፋልት መንገድ በተያዘው በጀት ዓመት አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የኮሪደር ልማት፣ የስማርት ሲቲ እና የዲጂታላይዜሽን ተግባራትን በማከናወን ከተማዋን ለማዘመን የተጀመረው ስራ ይጠናከራል ብለዋል።
የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ በባህር ዳር ከተማ እየተሰሩ ያሉ መሰረተ ልማቶች ከተማዋን ውብ፣ሳቢና ማራኪ ለማድረግ የሚያስችሉ ናቸው።
ይህም ከተማዋን ለቱሪዝም፣ለኢንቨስትመንት፣ ለኑሮና ለንግድ ተመራጭ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመው፥ ለስኬቱ ተገቢው ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል።
የክልሉን ሰላም ከማጽናት ጎን ለጎን ከተሞችን የሚያነቃቁ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፣የከተማ አመራሮች ተቀራራቢ ተልዕኮና እይታ ይዘው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የክልሉና የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በከተማዋ የሚገነቡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ተመልክተዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026