የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የካዴፕ የ10 ዓመት ስትራቴጂ እና የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ሆነ

May 6, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 27/2017 (ኢዜአ)፡-የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም (ካዴፕ) የ10 ዓመት ስትራቴጂ እና የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ማድረጊያ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ይፋ ሆኗል።


በስነ ስርዓቱ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የግብርና፣ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ፣የደቡብ አፍሪካ የግብርና ሚኒስትር ጆን ስቴንሁይሰን፣ የህብረቱ አመራሮች፣ የቀጣናዊ ተቋማት ኃላፊዎች፣የህብረቱ አባል ሀገራት ተወካዮች፣የልማት አጋሮች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።


በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ስትራቴጂው እና የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ማድረጋቸውን የአፍሪካ ህብረት ለኢዜአ በላከው መረጃ አስታውቋል።


ስትራቴጂው እና የማስፈጸሚያ የድርጊት መርሃ ግብሩ ከእ.አ.አ 2026 እስከ 2035 የሚቆይ ነው።


ዘላቂ ምርታማነትን፣አግሮ ኢንዱስትሪ እና ንግድን የበለጠ ማጠናከር፣ የኢንቨስትመንት መጠንን በማሳደግ የስነ ምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን ማሳለጥ እንዲሁም የምግብ እና የስርዓተ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ከስትራቴጂው ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።


ለዜጎች ሁሉን አካታች እና እኩል የሆነ የኑሮ ሁኔታን መፍጠር፣ የማይበገር ስርዓተ-ምግብ መገንባት እና የምግብ ስርዓት አስተዳደርን ማጠናከር ሌሎች የካዴፕ ግቦች ናቸው።


በስትራቴጂው የአፍሪካን የግብርና ምርታማነት እ.አ.አ በ2035 በ45 በመቶ ለማሳደግ እቅድ ተይዟል።


የአፍሪካ ህብረት ካዴፕን አስመልክቶ በጥር ወር 2017 ዓ.ም በዩጋንዳ ካምፓላ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አዲሱን የ10 ዓመት ስትራቴጂ ማፅደቁ የሚታወስ ነው።


የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዴፕ) የአጀንዳ 2063 አህጉራዊ ማዕቀፍ ሲሆን የአፍሪካ ሀገራት በግብርና መር ልማት ኢኮኖሚያቸውን በማሳደግ ረሃብን እንዲያስወግዱ እና ድህነትን እንዲቀንሱ ማድረግን ዋነኛ አላማው አድርጓል።


በካዴፕ አማካኝነት የአፍሪካ መንግስታት ከዓመታዊ ጥቅል ምርታቸው (ዲጂፒ) ቢያንስ 10 በመቶ የሚሆነውን ለግብርና እና ገጠር ልማት ለመመደብ ተስማምተዋል።


በዚህም ሀገራቱ የግብርና ዘርፉን በየዓመቱ ቢያንስ በስድስት በመቶ ለማሳደግ አቅደው በመስራት ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026