የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የክልሉ አርሶ አደሮች በቡና እና ቅመማ ቅመም ልማት የተሻለ ጥቅም እያገኙ ነው

May 7, 2025

IDOPRESS

ዱራሜ፤ሚያዝያ 28/2017(ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ዞኖች የሚገኙ አርሶ አደሮች በቡና እና ቅመማ ቅመም ልማት የተሻለ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።


ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ወደ 7 ሺህ ቶን የሚጠጋ የቡና እና የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡም ተገልጿል።


በከምባታ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ወንድሙ ሱጋሞ እንደገለፁት፥ በሁለት ሄክታር ማሳቸው ላይ ዝንጅብል ማልማት ከጀመሩ ሁለት ዓመታት አስቆጥረዋል፡፡


ዝንጅብልን በሄክታር እስከ አንድ መቶ ኩንታል እያመረቱ መሆኑን የገለፁት አርሶ አደሩ፥ ምርቱን ለገበያ በማቅረብም ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡


ሌላኛውና በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ አና በሌሳ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ግዛቸው በየነ፥ ከሌላ የግብርና ስራቸው ጎን ለጎን ቡና በማልማት ተጠቃሚ መሆን ከጀመሩ መሰንበታቸውን ተናግረዋል፡፡


በዚህ ዓመት በውስን መሬት እስከ አስር ኩንታል የቡና ምርት ማግኘታቸውንና ተጠቃሚነታቸውን ማሻሻል መቻላቸውን ጠቁመዋል፡፡


በተለይም የቡናው ዘርፍ ላይ መስራት የተሻለ ገቢ ለማግኘት እንደሚረዳ ያነሱት አርሶ አደሩ፥ ባላቸው የእርሻ ቦታ ላይ ቡናን በማልማት ተጠቃሚ ለመሆን እየሰሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡


የክልሉ ቡና እና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ቶፊቅ ጀዋር፤ በ2016/17 የምርት ዘመን በቡና እና የቅመማ ቅመም ምርቶች 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ መሰራቱን ተናግረዋል።


በምርት ዘመኑ እስካሁን 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል መገኘቱን ገልጸው ከዚህም 2 ሚሊዮን ኩንታሉ የዝንጅብል ምርት መሆኑን ጠቅሰዋል።


በክልሉ በዋናነት በርበሬ፣ሮዝመሪ፣ዝንጅብል፣ ኮሰረትን ጨምሮ ሌሎችም ጨምሮ የቡና እና ቅመማ ቅመም ምርቶችን ለማምረት የሚያስችል እምቅ አቅም ያለው መሆኑን ገልጸዋል።


በቡና ምርት ብቻ በተያዘው በጀት ዓመት 2 ሺህ 400 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ በዘጠኝ ወራት ብቻ 1 ሺህ 967 ቶን ቡና ማቅረብ ተችሏል ብለዋል።


በክልሉ በዚህ ዓመት ከበልግ ወቅት ጀምሮ እስከ ነሐሴ አጋማሽ የሚተከል ከ44 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ ለተከላ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026