የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ ላይ የግሉ ሴክተር ሚናውን በበቂ መጠን ሊወጣ ይገባል - የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት

May 7, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 28/2017(ኢዜአ)፡-በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ በተለይም የተግባር ልምምድ ላይ የግሉ ሴክተር ሚናውን በበቂ መጠን ሊወጣ እንደሚገባ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ገለጸ።

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስርዓተ ግንባታ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን በሚል አውደጥናት ተካሂዷል።

በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት መሪ ተመራማሪ ዶክተር አማረ ማተቡ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ ጥናት አቅርበዋል።

በጥናቱ የዘርፉ ዋና ዋና ችግሮች የተለዩ መሆኑን ገልጸዋል።

የግሉ ዘርፍ በተለይ ኢንዱስትሪው ሚናውን በበቂ ሁኔታ መወጣት ባለመቻሉ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ ላይ የተግባር ልምምድ ክፍተቶች መኖራቸውን ጥናቱ ያመለክታል ብለዋል።

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስርዓተ ትምህርቱ የገበያውን ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲከለስና ገበያው የሚፈልገውን ክህሎት ከማመላከት አንጻር ከግሉ ዘርፍ ብዙ ሰራዎች እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

የተግባር ልምምድ ስልጠና የሚሰጥባቸው ኢንዱስትሪዎች ለስልጠናው ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ስታንዳርዱን የጠበቀ ስልጠና ከመስጠትና ብቃት ያላቸውን አሰልጣኞች ከመመደብ አንጻር ሰፊ ክፍተቶች አሉ ብለዋል።

በመሆኑም በተግባር ልምምድ ስልጠናው ላይ የሚፈለገው ስኬት እንዳይገኝ ማድረጉን ተናግረዋል።

ዘርፉ ለተግባር ልምምድ ግብአቶችን፣ መሳሪያዎችን ለማሟላት ከፍተኛ በጀት የሚጠይቅ በመሆኑ የፋይናንስ እጥረት አንዱ ተግዳሮት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ለዚህም የግሉ ሴክተር ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባው አስረድተዋል።

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አማካሪ አቶ አዝመራ ከበደ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር የሚረጋገጠው ብቃት ያለው የሰው ሀይል ለኢንዱስትሪው ማቅረብ ሲቻል በመሆኑ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፉን ማሳደግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የግሉ ዘርፍ ተደራጅቶ የቴክኖሎጂና የሰው ሀይል ልማት ላይ በፖለሲ ተደግፎ እንዲሰራ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ትምህርትና ስልጠና ፖለሲ ክለሳ፣ ስትራቴጂ ዝግጅት፣ ተከታታይ የስራ ላይ ስልጠናዎች እንዲሁም የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026