አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት በማምረት ውጤታማ አንድንሆን አስችሎናል ሲሉ በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሚያዚያ 25 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆየውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከ288 በላይ አምራቾች እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡
ኢዜአ በቦታው በመገኘት ያነጋገራቸው በጨርቃጨርቅ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አምራቾች እንዳሉት ኤክስፖው ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡
የሮንሸንግ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ተወካይ እዝራ ዮሴፍ እንዳስታወቁት አሁን ላይ በንቅናቄው በመታገዝ ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት ጀምረዋል፡፡
ኤክስፖው አምራቾች እርስ በእርሳችን እንድንተዋወቅና የገበያ ትስስር እንድንፈጥር አስችሎናልም ነው ያሉት፡፡
የማርስ ዲዛይን መስራች እና ባለቤት ወይዘሮ ማርሳለም ሁሴን በበኩሏ፤ ኤክስፖው አምራቾችን የሚያገናኝ እና የገበያ ትስስር የሚፈጥር መሆኑን ተናግራለች፡፡
የሳዊን ጋርመንት መስራች እና ባለቤት አቶ ሽመልስ አስናቀ በኤክስፖው ከጥሬ ዕቃ አቅራቢዎችና የእኛን ምርት ከሚፈልጉ ነጋዴዎች ጋር ለመገናኘት ችለናል ብለዋል፡፡
የኤርኮ ታክስታይል ተወካይ አቶ ኤፍሬም በቀለ ከጨርቃጨርቅ ተረፈ ምርቶች የስፌት ክርና መሰል ግብዓቶችን እያመረቱ እንደሚገኙ ተናግሯል፡፡
አምራቾቹ አክለውም በተለይ እንደ ሀገር የውጭ ምንዛሪን በማዳን በኩል ተኪ ምርት በማምረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሮንሸንግ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ተወካይ እዝራ ዮሴፍ እንደ ሀገር የውጭ ምንዛሪ የሚያድኑ ተኪ ምርቶችን ለገበያ እያቀረብን እንገኛለን ብለዋል፡፡
የማርስ ዲዛይን መስራች እና ባለቤት ወይዘሮ ማርሳለም ሁሴን ኤክስፖው ምርታችንን በማስተዋወቅ ለውጭ ገበያ የምናቀርብበትን ዕድል ፈጥሮልናል ብላለች፡፡
የሳዊን ጋርመንት መስራች እና ባለቤት አቶ ሽመልስ አስናቀም ንቅናቄው ከውጭ ተመርተው ይመጡ የነበሩ ሸሚዞችንና የልጆች ንፅህና መጠበቂያ በሀገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሪ ማዳን ችለናል ነው ያሉት፡፡
በሀገር ውስጥ የምናመርተው ግብዓት ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በመተካት በኩል የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ሲሉ የተናገሩት ደግሞ የኤርኮ ቴክስታይል ተወካይ አቶ ኤፍሬም በቀለ ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025