የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በክልሉ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)

May 7, 2025

IDOPRESS

ቡታጅራ፤ ሚያዝያ 28/2017(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ገለጹ።

በክልሉ በምስራቅ ጉራጌ ዞን የተለያዩ መዋቅሮች ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።


የመስኖ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድ፣ የዘመናዊ ተንጠልጣይ ድልድይና የመደበኛ ድልድዮች ግንባታ ሥራዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ከተደረጉት መካከል ይገኙበታል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንደገለጹት መንግሥት ከዜጎች የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።

በዚህም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዱ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ወስጥ ገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን ገልጸዋል።


ከእነዚህ ውስጥ ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ ፕሮጀክቶችን ለአብነት አንስተዋል።

በክልሉ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡


የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር ኢ/ር) በበኩላቸው መንግስት የዜጎችን የልማት ጥያቄዎች በፍትሃዊነት ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ሚኒስቴሩ በክልሉ በመንግስትና በአጋር አካላት ትብብር ከ7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ 44 የመስኖና የንፁህ መጠጥ ውሃን ተደራሽ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።


በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ መሀመድ ኑርዬ(ዶ/ር) በበኩላቸው ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁት ፕሮጀክቶች መንግሥት ለዜጎች ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ያለውን ተነሳሽነት የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ተገንብተው ዛሬ ለአገልግሎት የበቁት ፕሮጀክቶች ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ምርታማነትን ለማሳደግና የአርሶ አደሩን ምርትን ወደ ገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

በፕሮጀክቶች የምረቃ መርሃ ግብር ላይ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ከተመረቁት የልማት ፕሮጀክቶች በተጨማሪ በ500 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው የቡታጅራ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክት የመሰረተ ድንጋይ በርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) እና በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር ኢ/ር) እንደተቀመጠ መዘገቡ ይተወሳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026