አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪው በተኪ ምርትና በስራ ዕድል ፈጠራ ገንቢ ሚና እንዲወጣ ማገዙን አምራቾች ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ መርቀው መክፈታቸው ይታወሳል።
ኢዜአ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው የቀረቡ አምራቾችን ተዘዋውሮ አነጋግሯል።
የኢናስ ሶሊሽን ተወካይ ዮናስ ሸዋንግዛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርታማነት በማሳደግና በሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።
ፋብሪካቸው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚጠይቀውን ብረት በአገር ውስጥ በማምረት ተስፋ ሰጪ አቅም እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የሸንጋይ ማሽነሪ ሥራ አስፈፃሚ ብርቱካን ጌታሁን በበኩላቸው ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከፍተኛ አቅም የሚሆኑ የግንባታ ማሽነሪ እያመረቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪው የተሰጠው ትኩረት በተኪ ምርትና በስራ ዕድል ፈጠራ ገንቢ ሚና እንዲወጡ እያስቻላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ኤክስፖው በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ የብረታ ብረት ውጤቶችን በማስተዋወቅ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የፔጋስ ኢንጂነሪንግ ተወካይ ሰለሞን ታደሰ ተናግረዋል።
ድርጅታቸው ከውጭ የሚገቡ የተሽከርካሪ አካላትን በሀገር ውስጥ በማምረት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀው በቀጣይም በተኪ ምርት ላይ በስፋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
የዲኬ ኦልድ ኩባንያ ተወካይ ወይዘሮ የምስራች ንጋቱ ኤክስፖው ምርትና አገልግሎታቸውን በማስተዋወቅ የገበያ ትስስር የሚያገኙበትን መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን አስረድተዋል።
ንቅናቄው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት ከማስቻሉ በላይ ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር የራሱን ሚና መጫወቱን አስረድተዋል፡፡
መንግስት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዘርፉን ለማበረታታት እያደረገ የሚገኘው ድጋፍና ክትትል የምርታማነት አቅማቸውን ለማሳደግ ከፍተኛ ዕገዛ እያደረገላቸው እንደሚገኝ አስተያየት ሰጪዎቹ አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025