
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2017(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባን የልማትና የሰላም ምሳሌነት ለማስቀጠል የሰላም ሰራዊት አባላት የላቀ ሚናቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በተግባርና ንድፈ ሐሳብ ያሰለጠናቸውን 11 ሺህ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት አስመርቋል።
በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ እንደገለጹት፤ በፓርቲው አመራርና የህዝቡ ተሳትፎ አዲስ አበባን ውብ፣ ጽዱ እና ዓለም-አቀፍ የከተማ ስታንዳርድ እንድታሟላ እየተደረገ ነው።
ፓርቲው ባለፉት የለውጥ ዓመታት በህዝብ የተጣለበትን ኃላፊነት እና የገባቸውን ቃሎች በተግባር በመፈጸም ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በተግባር አሳይቷል ብለዋል፡፡
በመዲናዋ ለሰው ተኮር ተግባራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፥ የህዝቡ ተሳትፎ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የመዲናዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሰላም ሰራዊት አባላት ከመደበኛ የፀጥታ ተቋማት ጋር እያደረጉት ያለው ቅንጅታዊ ስራ አበረታች እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
በዚህም የፀረ ሰላም ኃይሎችን እኩይ ተግባር ቀድሞ ማክሽፍ እና ከምንጩ ማድረቅ መቻሉን ገልጸው፥ የዛሬ ተመራቂዎችም ከተማዋን የልማትና የሰላም ምሳሌ አድርጎ ማስቀጠል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው፤ የመዲናዋን ፈጣን እድገት ለማስቀጠል አስተማማኝ ሰላምን ማስፈን የግድ መሆኑን ገልጸዋል።
ከተማ አስተዳደሩ የህዝብን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያረጋገጠ የሰላም ሰራዊት በመገንባት የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
ዛሬ ከተረመቁ የሰላም ሰራዊት አባላት መካከል ሻለቃ ብርሐኑ በቀለ፥ በወሰዱት የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና መሰረት አካባቢያቸውን በንቃት ለመጠበቅ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
ሌላኛዋ ተመራቂ ትዕግስት አበጋዝ በበኩላቸው፥በስልጠና ቆይታቸው ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ሰላምን ለማስጠበቅ የሚያስችል እውቀት ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ለጸጥታ ኃይሉ አጋዥ ሆነን የአካባቢያችንን ሰላም ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ ተዘጋጅተናል ያሉት ደግሞ አቶ ያለው ታደሰ ናቸው፡፡
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026