ዲላ፤ ግንቦት 3/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት 10 ወራት በክልሉ ከሚገኙ ሦስት ሐይቆች 23 ሺህ ቶን የሚጠጋ የዓሳ ምርት ለገበያ መቅረቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል።
በጓሯቸው ኩሬ በመገንባት የጀመሩት የዓሣ እርባታ የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ የስነ ምግብ ይዘትን ለማሻሻል እየረዳቸው መሆኑን በክለሉ የጌዴኦ ዞን አርሶ አደሮች ገልጸዋል።
በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳት ዝሪያ ማሻሻያ ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሃብተጊዮርጊስ ባለፉት 10 ወራት በክልሉ ከሚገኙ ሦስት ሐይቆች 23 ሺህ ቶን የሚጠጋ የዓሳ ምርት ለገበያ መቅረቡን ተናግረዋል።
የዓሳ ሃብት አቅም ወደ ሁሉም የክልሉ ወረዳዎች በማስፋት የስነ ምግብ ይዘትን ለማሻሻል በተደረገ ጥረት በአሁኑ ወቅት 350 አነስተኛ ኩሬዎችን በአርሶ አደር ጓሮ መገንባት መቻሉን ነው ያነሱት።
ከዚህ ውስጥ በ275 ኩሬዎች ውስጥ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ የዓሳ ጫጩቶችን በማሰራጨት የማርባትና የማባዛት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጨምረው ተናግረዋል።
ይህም የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ የስነ ምግብ ይዘትን እያሻሻለ ነው ብለዋል።
በጓሯቸው ኩሬ በመገንባት የጀመሩት የዓሣ እርባታ የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ የስነ ምግብ ይዘትን ለማሻሻል እየረዳቸው መሆኑን በክልሉ የጌዴኦ ዞን አርሶ አደሮች ገልጸዋል።
በዓሳ ልማቱ ተሳታፊ ከሆኑት አርሶ አደሮች መካከል በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ነዋሪው በቀለ ዱካሌ ለኢዜአ እንደገለጹት ከእርሻ ልማት ጎን ለጎን በጓሯቸው በቆፈሩት ኩሬ የዓሳ ልማት እያከናወኑ ነው።
ባለፉት ስድስት ወራት ከ1ሺህ በላይ የዓሣ ጫጩቶችን ከመንግስት በድጋፍ በመረከብ እያረቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ለምግብነት የደረሱ ዓሳዎችን በማውጣት እየተጠቀሙ መሆኑን ጠቅሰው ይህም በቤተሰብ ደረጃ የስነ ምግብ ይዘትን እንዳሻሻለላቸው አንስተዋል።
አካባቢያቸው ውሃ ገብ ከመሆኑ ባለፈ ለዓሳ መኖ የሚሆን ቅጠላቅጠል በስፋት እንደሚገኝ ያነሱት አርሶ አደሩ፤ እድሉን ተጠቅመው በስፋት በማርባት በቀጣይ ለገበያ ለማቅረብ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአካባቢያቸው የተገነባው የኢላልቻ የመስኖ አውታር የፈጠረላቸው ሁለት ኩሬዎች ከመስኖ ልማት ጎን ለጎን ወደ ዓሳ እርባታ እንደገቡ ያነሱት ደግሞ በዞኑ ቡሌ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ፈቂ ከድር ናቸው።
ባለፈው ዓመት ከሁለት ሺህ በላይ ዓሳዎችን በማርባት የምግብ ፍጆታቸውንና ለአካባቢው ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተያዘው ዓመት ከ2ሺህ 500 በላይ ዓሳዎችን በመረከብና በማርባት ምርቱን መጠቀም መጀመራቸውን ተናግረዋል።
በወረዳው በዘጠኝ ኩሬዎች ዓሳን በአርሶ አደሮች ጓሮ የማልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የቡሌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት የአሳና እንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ማርያም ጂክሶ ናቸው።
በተለይም በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የዓሳ መንደር ምስረታ በማከናወን አርሶ አደሩ በስፋት ወደ አሳ ልማት እንዲገባ የዓሳ ጫጩት፣ የኩሬ ግንበታና የክህሎት ስልጠና ድጋፎች እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ውሃ ገብ በሆኑ አካባቢዎች አርሶ አደሩ ዓሳ አርብቶ ለምግብ ፍጆታ እንዲጠቀም እድል መፍጠሩን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025