የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በአማራ ክልል 28 የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታን ማጠናቀቅ ተችሏል

May 12, 2025

IDOPRESS

ባህር ዳር፤ ግንቦት 3/2017 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ በመገንባት ላይ ከነበሩ የመስኖ ፕሮጀክቶች 28ቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት መዘጋጀታቸውን የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ዳኝነት ፈንታ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት ክልሉ ያለውን ዕምቅ የውሃ ሃብት በአግባቡ በመጠቀም በበጋ መስኖ ልማት የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።

ለዚህም በዘንድሮው በጀት ዓመት የክልሉ መንግስት በመደበው 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የ154 የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ከእነዚህ ውስጥ የ95 ፕሮጀክቶችን ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት አጠናቆ በቀጣይ ዓመት የበጋ ወቅት ከ4ሺህ 500 ሄክታር በላይ ተጨማሪ መሬት በአዲስ መስኖ ወደልማት ለማስገባት ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።


ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተደረገው ጥረት የ28 ፕሮጀክቶች ግንባታ ስራ ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ መቻሉን አስታውቀዋል።

ሰላምን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን እየተከናወነ ባለው የልማት ስራ አንዳንድ ፕሮጀክቶች እስከ ሃያ ወራት ሊወስዱ ይችሉ የነበረውን የግንባታ ጊዜ በተቋራጮች ቁርጠኝነትና በቢሮው ድጋፍና ክትትል ከአምስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ለማጠናቀቅ መቻሉን ጠቁመዋል።

በግንባታ ላይ የሚገኙ ሁሉም የመስኖ ፕሮጀክቶች በቀጣይ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቁ በአዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶቹ ብቻ 23 ሺህ ሄክታር ተጨማሪ መሬት በማልማት በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ሂደት እንደሚያግዙ አስታውቀዋል።

እንዲሁም ቀደም ሲል ተገንብተው በአጠቃቀምና በአያያዝ ችግር ምክንያት ተበላሽተው አገልግሎት አቋርጠው የቆዩ ከሃያ በላይ ነባር የመስኖ ፕሮጀክቶች ጥገና ስራም እየተከናወነ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አስታውቀዋል።


እየተከናወኑ በሚገኙ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታና ጥገና ስራ ከ23 ሺህ ለሚበልጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025