
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 3/2017(ኢዜአ)፦ በአፋር ክልል በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚሰማሩ ኢንቨስተሮች ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በክልሉ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመለየት ወደ ስራ ተገብቷል።
ከተለዩት የኢንቨስትመንት አማራጮች መካከልም የተለያዩ የተፈጥሮ ማዕድናት ሀብቶች ተጠቃሽ ናቸው።
ይህንንም ተከትሎ ኢንቨስተሮች በክልሉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
በዚህም የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እየተሰማሩ መሆኑንና በተሰማሩበት ዘርፍም ውጤታማ እየሆኑ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
ከክልሉ የተለያዩ ምርቶች ወደ ውጭ እየተላኩ መሆኑን አንስተው፤ የኮፐር ማዕድን ምርት በሙከራ ደረጃ ወደ ውጭ መላክ መጀመሩን ለአብነት ጠቅሰዋል።
በቀጣይም ሌሎች ምርቶችን ለመላክ እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡
ከ10 በላይ የውጭ ካምፓኒዎች በግብርና ልማት፣ በሪል ስቴት ግንባታ፣ በኬሚካል ኢንዱስትሪ እና በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውንም ተናግረዋል።
በክልሉ የኮሪደር ልማት መጀመሩ ኢንቨስትመንት በመሳብ ረገድ ትልቅ ድርሻ ያለው መሆኑንና ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በክልሉ የሚገኙ ጸጋዎችን የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝና ህብረተሰቡን ከኢንቨስትመንቱ ተጠቃሚ በማድረግ በኩል ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026