
አዲስ አበባ፤ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ በወሰደቻቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን ለማሳካት በትክክለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።
በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በፎረሙ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በርካታ የለውጥ እርምጃ እየወሰደች መሆኑን ገልጸዋል።
የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችም እድገትን ለማስቀጠል፣የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና መዋቅራዊ ሽግግርን ለማሳካት እንደሚያስችሉ ተናግረዋል።
ይህም ኢትዮጵያ በትክክለኛው የዕድገት ጎዳና ላይ እንድትገኝ አድርጓታል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ብሩህ መሆኑን ገልጸዋል።
የማበረታቻ ስርዓቶችም ባለሀብቶች ኢንቨስትመንታቸውን እንዲያስፋፉና ዘላቂነትን እንዲያረጋግጡ የሚያግዙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ፎረሙ ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አቅም ለማሳየት ትልቅ ዕድል መሆኑን ጠቅሰው፤ የመድረኩ ተሳታፊዎች የተሻሉ ልምዶችን እንዲለዋወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የተሻለ አድል ለማግኘት በሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረጓን ገልጸዋል።
ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ ሆነው የቆዩ ዘርፎችን የመክፈት ሀገራዊ ሪፎርም፣ የህግና የፖሊሲ ማሻሻያዎች እና በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ ተጨባጭ ለውጦች ማምጣታቸውን አንስተዋል።
እንዲሁም ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆኑ መሰረተ ልማቶች እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው መስኮች ለሚሰማሩ በርካታ ማሻሻያዎችን ማድረጓን ጠቁመዋል።
በብዙ የበለጸጉ አገራት የውጭ ባለሀብቶች ስኬት በሦስት ምክንያቶች ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን አንስተዋል።
ይህም የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ እውቀት መስፋፋት እና የገበያ ትስስር መሆኑን ገልጸው፤ የኢትዮጵያ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ከአህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ የአቅርቦት ሰንሰለት ጋር ማቀናጀት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ይህም ኢንቨስተሮች የረጅም ጊዜ እና ዘላቂ ኢንቨስትመንትን ለማረጋገጥ በጣም ወሳኝ መሆኑንም አመልክተዋል።
ዱራሜ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግብርና ዘርፍ ያሉ ፀጋዎችን ለልማት በማዋል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ሥ...
Jun 6, 2026
ደሎ መና፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የአርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያግዙ ዘመናዊ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑ...
May 26, 2026
ጋቼኖ ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም እንደሚገባ የክ...
May 21, 2026
አሶሳ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክ...
Apr 29, 2026