አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፦ ነባርና አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችን በማልማት ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።
ቋሚ ኮሚቴው የቱሪዝም ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
በግምገማው ከቱሪስት መዳረሻ ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና ጎብኚዎችን የመሳብ ሥራዎች ዙሪያ ትኩረት ያደረጉ ጥያቄዎች ቀርበው በሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር አንድ ሚሊዮን ለማደረስ ግብ ተጥሎ ርብርብ ተደርጓል።
በዚህም በዘጠኝ ወራት በተከናወኑ ተግባራት 942ሺህ 407 ጎብኚዎች መምጣታቸውን ጠቁመው፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ አፈጻጸም የተመዘገበበት ነው ብለዋል።
ለ100ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ከ80ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በሆቴሎች፣ በቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች፣ በአስጎብኚ ድርጅቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩንም አብራርተዋል።
በበጀት ዓመቱ የሆቴሎችን ደረጃ የመመደብ ተግባራት መከናወናቸውንም ጨምረው ተናግረዋል።
ለባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት ወደ ሥራ የማስገባቱ ሥራም ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላትን እምቅ ሃብት በተለያዩ አማራጮች የማስተዋወቅ ተግባራት በሰፊው እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ከውጭ ምንዛሬ ግኝት አኳያም ዘርፉ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ እያደገ ሲሆን፤ በቀጣይም የውጭ ምንዛሬ ግኝቱን ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው፤ ሚኒስቴሩ የቱሪስት መስህብ ቦታዎችን ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው።
ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ብሄራዊ ፓርኮች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እየተገነባላቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበርም የኔት ወርክ አገልግሎት የሌለባቸው መዳረሻዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የውጭ ጎብኚዎችን ፍሰት መጨመር የሚያስችል ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ሥራ መገባቱን አብራርተዋል።
በዚህም በመካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም ላቲን አሜሪካ ሀገራት ጎብኚዎችን ለመሳብ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ነው ያሉት።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አይሻ ያህያ እንዳሉት፤ ነባርና አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችን በማልማት ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው።
በቱሪዝም ዘርፍ ኢንቨስትመንት የመሳብ ሥራ በትኩረት ሊከናወን እንደሚገባ ጠቁመው፤ እምቅ ሃብቶችን ይበልጥ በማስተዋወቅ ከዘርፉ የተሻለ ጥቅም እንዲገኝ መሥራት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025