ሆሳዕና፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፦ የአምራች ዘርፉን እንቅስቃሴ በመደገፍና በማገዝ የተኪ ምርት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በክልሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተዘጋጀ የማኑፋክቸሪንግ ውጤቶች ባዛርና ኤግዚቢሽን በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል፡፡
በዚሁ መርሃ ግብር ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር )፤ በክልሉ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ስኬታማ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
ዘርፉ ተኪ ምርቶችን በስፋት በማምረት ኢኮኖሚውን ለመደገፍና የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለመቀነስ ጉልህ ድርሻ ያለው መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም የአምራች ዘርፉን እንቅስቃሴ በመደገፍና በማገዝ የተኪ ምርት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ታምራት ንቅናቄ በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች ስራ ያቆሙ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲነቃቁ ማድረጉን ጠቁመው በዚህም በርካታ ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
በክልሉ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በማጠናከር ሁሉ አቀፍ ውጤት ለማስመዝገብ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የኮርፖሬሽኑ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለዘርፉ መነሳሳት የላቀ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።
በመሆኑም ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የገበያ ትስስር በመፍጠር የምርት ሂደቱን ለማሳለጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የክልሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ናትናኤል ሚሊየን በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ተኪ ምርቶችን በማምረት የክልሉን ገቢ ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል፡፡
ኢንዱስትሪዎቹ የግብርና ምርቶች ላይ ዕሴት በመጨመር በኩል አበረታች እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ ሲሆን ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025