ነቀምቴ፤ግንቦት 7/2017(ኢዜአ)፦በነቀምቴ ከተማ በ464 ሚሊዮን ብር እየተካሄዱ የሚገኙ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ገለፀ።
የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የመሰረተ ልማት ስራዎች ቡድን መሪ አቶ ደረጄ ዶጃ እንደገለጹት በከተማው ነዋሪውን ተጠቃሚ ያደረጉ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው።
በተያዘው በጀት ዓመትም 37 የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ በ464 ሚሊዮን ብር እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ከልማት ስራዎቹ መካከል የኮብልስቶን ድንጋይ ንጣፍ እና እድሳት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮች፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ግንባታና ከፈታ፣ የመንገድ ዳር መብራቶች ተከላ፣ የውሃ መስመር ዝርጋታ እና ሌሎች ስራዎች ይገኙበታል ብለዋል።
ከግብርና ኢኒሼቲቭ አንጻርም ለከብት ለማደለብ፣ ለዶሮ እርባታ፣ ለወተት ላሞች እርባታ፣ ለጎጆ ኢንዱስትሪ እና ለመኖ ማዘጋጃ የሚውሉ ሼዶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል።
የመሰረተ ልማት ስራዎቹ ሲጠናቀቁ በርካታ የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሲሆን ለበርካታ ወጣቶችም የስራ እድል መፍጠራቸውን ጠቅሰዋል።
ከግንባታ ሂደቱም ባለፈ በከተማዋ በተገነቡ የዶሮ እርባታ እና የበሬ ማደለቢያ ሼዶች ወጣቶች ተደራጅተው የስራ እድል ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
በግንባታ ላይ የመሚገኙ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች አብዛኞች መጠናቀቃቸውን ገልጸው ቀሪዎቹን የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት አጠናቆ ለህዝብ አገልግሎት ለማዋል ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በከተማው በተገነቡ ሼዶች የስራ እድል ከተፈጠረላቸው መካከል የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ መደበኛ ህይወት የተቀላቀሉ ወጣቶች ይገኙበታል።
ከነዚህም መካከል ወጣት ደበላ መርጋ፤ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር በማህበር በመደራጀት በዶሮ እርባታ ስራ ላይ መሰማራታቸውን ገልጿል።
ለዚህም ከከተማ አስተዳደሩ ከገንዘብ ጀምሮ አስፈላጊ ድጋፍ ማግኘታቸውን ጠቁሞ ባገኙት ሰርተው ለመለወጥ እየተጉ መሆኑን ተናግሯል።
በተመሳሳይም የተሃድሶ ስልጠና ወስዶ የስራ እድል የተፈጠረለት ወጣት ኬንቦን ቀነአ፤ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር በመሆን ከብት በማደለብ ስራ ላይ መሰማራቱን ይናገራል።
በቀጣይም ባገኙት እድል የተሻለ ተጠቃሚ ለመሆንና ህይወታቸውን ለመቀየር እንደሚተጉም ጠቁሟል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025