አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እውን ለማድረግ በሁሉም ዘርፍ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ።
ሚኒስትር ዴኤታው የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እውን ለማድረግ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም መንግሥት ለሰላም ትኩረት በመስጠት ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመለሱ ግማሽ መንገድ ድረስ ተጉዞ በመቀበል ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል ብለዋል።
ከዚህም ባሻገር የሰላም ጥሪውን በማይቀበሉ ቡድኖች ላይ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ውጤታማ የህግ ማስከበር ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግስት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ቱሪዝም፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፎች ባከናወናቸው ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
መንግሥት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በመስኖ ስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት እና በሌሎችም ዘርፎች እመርታዊ ለውጦች መታየታቸውን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ በበጋ ስንዴ ልማት ሶስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን ከ66 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።
የበልግ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈን መቻሉን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ 235 ሺህ ሄክታር በኩታ ገጠም መልማቱን ተናግረዋል።
መንግስት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በምግብ እህል ራስን ለመቻል የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እና ምርጥ ዘር ስርጭትን ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በ2017/18 የምርት ዘመን ለአፈር ማዳበሪያ ግዢ አንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ዶላር መመደቡን አስታወሰው፣ 84 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅምና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት መጨመሩን ገልጸዋል።
በዚህም ባለፉት ሶስት ዓመታት 10 ነጥብ 34 ቢሊዮን ዶላር ግምት ያለው የውጭ ምርት መተካት ተችሏል ብለዋል።
መንግሥት የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ለማሳደግ ነባር የቱሪስት መዳረሻዎችን በማደስና አዳዲስ መዳረሻዎችን በመገንባት ስኬታማ ስራ ማከናወኑን ገልጸዋል።
ባለፉት አስር ወራት ብቻ 84 ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን በብቃት በማከናወን ከ30 ሺህ በላይ የውጭና ከ171 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ማሳተፍ ተችሏል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025