
አዲስ አበባ፤ግንቦት 10/2017 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ እያከናወነች ያለችውን ውጤታማ ተግባራት ያሳየችበት መሆኑ ተገለፀ።
በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 ተጠናቋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሀሚድ እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የኤክስፖውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም፥ በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 በዲጂታላይዜሽን እና በቴክኖሎጂ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለዓለም ማስተዋወቅና በርካታ ትስስር መፍጠር ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሀሚድ፥ በኤክስፖው ከ15 ሺህ በላይ ታዳሚዎች መሣተፋቸውን ተናግረዋል።
ኤክስፖ 2025 የሳይበር ደህንነት፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የፋይናንስ ደህንነት፣ ስማርት ሲቲ እና የቴክኖሎጂ ትምህርት ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህም አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በዓይነቱ ልዩ በሆነው ኤክስፖ 2025 ከመንግሥት፣ ከግል እና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተወጣጡ ኩባንያዎች መሣተፋቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኤክስፖ 2025 በርካታ ወጣቶች እንዲነቃቁ ያደረገ ነው ብለዋል።
ከ100 በላይ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኤክስፖ 2025 መሣተፋቸውን ጠቁመው፤ የተለያዩ ውድድሮች ተካሂደው ኢትዮጵያውያን ማሸነፋቸውን ተናግረዋል።
ኤክስፖው ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያለችበትን ደረጃ ያሳየችበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፍ ኤክስፖ 2025 ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ እያከናወነች ያለችውን ውጤታማ ተግባራት ያሳየችበት መሆኑንም ተናግረዋል።
ኤክስፖው ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ያስመዘገበቻቸው ስኬቶችን እና በዲጂታል ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለዓለም ያስተዋወቀችበት ነውም ተብሏል።
በኤክስፖው የተለያዩ ጥናቶች የቀረቡበት፣ የፓናል ውይይቶች እንዲሁም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሮቦቲክስ ውድድሮች የተካሄዱበት ነበር።
ይህ በኢትዮጵያ የተሰናዳው ዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 በሁሉም መስክ የምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የቴክኖሎጂ ሁነት ነው።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026